Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dmv

Department of Motor Vehicles
 

DC Agency Top Menu

-DC DMV will no longer prevent DC residents from applying for a new or renewed driver’s license because of failing to meet the requirements of the Clean Hands Law.

-A +A
Bookmark and Share

Driver Services Amharic

የነጂዎች አገልግሎቶች

የነጂ አገልግሎቶች ለዲስትሪክት ነዋሪዎች የፈቃድ እና የመታወቂያ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

የመንጃ ፈቃድ 
የለማጅ ፈቃድ
የመሸጋገሪያ ፈቃድ
የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ ወረቀት
የማንነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ማረጋገጫ
የነዋሪነት ማረጋገጫ
የመንዳት ችሎታ ማረጋገጫ
የአድራሻ ለውጥ
የነጂ መዝገብ(ሪከርድ)
ሞተርሳይክል ፈቃድ
የህክምና(የጤና)መስፈርቶች 
የጉዳተኞች ታርጋ እና ምልክት ማሳያ
የመንዳት ፈተና (እውቀት፣ ችሎታ አና  ሞተርሳይክል)
የግራድ (GRAD) ፕሮግራም
የአካል እና ቲሹ ለጋሽ
አግባብ ያላቸው ክፍያዎች
ሌላ የነጂ አገልግሎቶች መረጃ 
የነጅ አገልግሎቶች ቅጾች እና ኦንላይን(የኢንተርኔት ላይ) ማስፈጸሚያ(ግብይት)

 

የመንጃ ፈቃድ <<ወደላይ መመለስ>>

ከሜይ 1፣ 2014 ጀምሮ ዲሲ ዲኤምቪ የሪል መታወቂያ (REAL ID) የመንጃ ፈቃድ እና የመታወቂያ ወረቀት (ID) እና ለተወሰነ ጉዳዮች የሚያገለግል የመንጃ ፈቃዶች እና የመታወቂያ ወረቀትን (ID) ማተም ይጀምራል ። 

ለሪል መታወቂያ (REAL ID) ማረጋገጫ ዋናው መስፈርቶች በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ህጋዊ ቆይታ እንዳሎት ማስረጃ፣ ማንነቶን የሚያሳይ ማስረጃ (ስም እና የትውልድ ቀንን ያካትታል) ፣ የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ (ወይም ለሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ብቁ እንዳልሆኑ የሚጠቁም ደብዳቤ) እና የነዋሪነት ማረጋገጫ። የሪል መታወቂያ (REAL ID) የዲሲ ዲኤምቪ (DC DMV) የማስረጃ ወረቀቶትን በሙሉ እንደገና ማጽደቅ እንዳለበት ያስገድደዋል።

ለተወሰነ ጉዳዮች (Limited Purpose) ለሚያገለግል ማረጋገጫ ዋናው መስፈርቶች ማንነቶን የሚያሳይ ማስረጃ(ስም እና የትውልድ ቀንን ያካትታል)፣ የአሁኑ ወቅት የዲሲ የነዋሪነቶ ማረጋገጫ፣ የ6-ወራት የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ እና የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር መቼም ታትሞለት እንደማያውቅ፣ የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ተሰጥቶት ነበር ነገር ግን አሁን ማመልከቻውን ባቀረቡበት ግዜ የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ለመቀበል ብቁ አለመሆኖኑ ወይም የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ለመቀበል ብቁ እንዳይደሉ የሚያሳይ ማስረጃ ነው።

የሪል መታወቂያ (REAL ID) የመንጃ ፈቃድ ማግኘት - የእውቀት ፈተና ፣ የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተና ወስደው ይለፉ እና የብቁነት መስፈርቶችን ያሟሉ። 

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(ማገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
• የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
• የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር
• የወላጅ ፈቃድ ማረጋገጫ (እድሜያቸው 16 ወይም 17 አመት ከሆነ)

ከሌላ ስቴት የሆነውን የመንጃ ፈቃድ መቀየር – ዲሲ ውስጥ ከ 30 ቀናት በላይ ነዋሪ ከሆኑ እና የብቁነት መስፈርቶቹን ካሟሉ፣ ከሌላ ስቴት የሆነውን የመንጃ ፈቃድ ለዲሲ ዲኤምቪ ያቅርቡ።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(ማገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ                                                         
የመንዳት ችሎታ ማረጋገጫ
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር
• የወላጅ ፈቃድ ማረጋገጫ (እድሜያቸው 16 ወይም 17 አመት ከሆነ)

ከአገር ውጪ በሆነ የመንጃ ፈቃድ የሪል መታወቂያ (REAL ID) መንጃ ፈቃድ ማግኘት –
የዩ.ኤስ. ዜጋ ያልሆኑ፣ ዲሲ ውስጥ ከ 30 ቀናት በላይ ነዋሪ ከሆኑ እና የብቁነት መስፈርቶቹን ካሟሉ፣ ቀኑ ያልተቃጠለ የውጭ አገር የሆነ የመንጃ ፈቃድ ለዲሲ ዲኤምቪ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ከውጭ አገር የሆነውን የመንጃ ፈቃዶን እርሶ ጋር እንዲያስቀሩት ይፈቀድሎታል። የመንዳት የእውቀት ፈተና ማለፍ አለቦት። 

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(ማገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ                                                         
የመንዳት ችሎታ ማረጋገጫ
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር
• የወላጅ ፈቃድ ማረጋገጫ (እድሜያቸው 16 ወይም 17 አመት ከሆነ)

ለተወሰነ ጉዳይ የሚያገለግል የመንጃ ፈቃድ ማግኘት – የእውቀት ፈተና  እና የጎዳና ላይ ፈተና መውሰድ እና ማለፍ፣ እና የብቁነት መስፈርቶቹን ማሟላት። ለተወሰነ ጉዳይ የሚያገለግል የለማጅ ፈቃድን (Limited Purpose learner permit) ለማግኘት [ቀጠሮ]ማስያዝ አለቦት። የእውቀት ፈተና እንዲወስዱ ስለሚጠየቁ፣ ከዲኤምቪ (DMV) ቀጠሮዎ በፉትየመንዳት መማሪያ ማንዋሉን ማጥናቶን እና ማየቶን ያረጋግጡ።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(ማገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ ማስረጃ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
ዲሲ ውስጥ 6-ወራት እንደኖሩ ማረጋገጫ                                                        
ሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር (SSN) መግለጫ (ማረጋገጫ) ቅጽ
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር
• የወላጅ ፈቃድ ማረጋገጫ (እድሜያቸው 16 ወይም 17 አመት ከሆነ)

የመንጃ ፈቃድ ማደስ – የዲሲ ሪል መታወቂያ (DC REAL ID)  የመንጃ ፈቃድ (ከላይ በቀኝ በኩል ኮኮብ ያለበት) ገና ከሌሎት፣ የዲኤምቪ የአገልግሎት መስጫ ማእከልን መጎብኘት አለቦት።ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች (ማገናኛ)በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ። የዲሲ ሪል መታወቂያ (DC REAL ID)  የመንጃ ፈቃድ ወይም ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግለው የመንጃ ፈቃድ (Limited Purpose driver license) ካሎት፣ በኢንተርኔት(ኦን ላይን) ለማደስ ብቁ ይሆኑ ይሆናል።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ                                                                                                                  
• ቀኑ የሚቃጠለው የዲሲ የመንጃ ፈቃድ   

የመንጃ ፈቃድን መተካት – የዲኤምቪ (DMV)  የአገልግሎት መስጫ ማእከልን ይጎብኙ ወይም ግልባጭ/መተኪያ የመንጃ ፈቃዶን በኢንተርኔት(ኦንላይን) ያግኙ።፡ኦንላይን ለማስፈጸም(ለመገበያየት) የዲሲ ሪል መታወቂያ (DC REAL ID)  የመንጃ ፈቃድ (ከላይ በቀኝ በኩል ኮኮብ ያለበት) ወይም ለተወሰነ ጉዳዮች የሚያገለግል (Limited Purpose) የመንጃ ፈቃድ ባለይዞታ መሆን አለቦት። ግልባጭ ለማግኘት ወደ ዲኤምቪ የአገልግሎት መስጫ ማእከል ከሄዱ እና የዲሲ ሪል መታወቂያ የመንጃ ፈቃድ ወይም ለተወሰነ ጉዳዮች የሚያገለግል የመንጃ ፋቃድ ከሌሎት፣ ከታች መስፈርቶች ስር የተቀመጡትን ተጨማሪ ነገሮች ማምጣት አለቦት። የዲሲ ሪል መታወቂያ መንጃ ፈቃድ ወይም ተለወሰነ ጉዳይ የሚያገለግል የመንጃ ፈቃድ ካሎት፣ ግልባጭን ኦንላይን ለመጠየቅ ብቁ ይሆኑ ይሆናል።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የሪል መታወቂያ (REAL ID) የማንነት ማረጋገጫ
የሪል መታወቂያ (REAL ID) የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ    
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ

ወይም

ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግል (Limited Purpose) የማንነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ

 

የለማጅ ፈቃድ <<ወደላይ መመለስ>>

የሪል መታወቂያ (REAL ID) የለማጅ ፈቃድ ማግኘት - የእውቀት ፈተና መውሰድ እና ማለፍ እና የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላት።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር
• የወላጅ ፈቃድ ማረጋገጫ (እድሜያቸው 16 ወይም 17 አመት ከሆነ)

ለተወሰነ ነገሮች የሚያገለግል የለማጅ ፈቃድ ማግኘት- የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተናን መውሰድ እና ማለፍ እና የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላት አለቦት። ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግሉን የለማጅ ፈቃድን ለማግኘት ቀጠሮ ማስያዝ አለቦት። የእውቀት ፈተና እንዲወስዱ ስለሚጠየቁ፣ ከዲኤምቪ ቀጠሮዎ በፉት የመንዳት መማሪያ ማንዋሉን ማጥናቶን እና ማየቶን ያረጋግጡ።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(ማገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
ዲሲ ውስጥ 6-ወራት እንደኖሩ ማረጋገጫ                                                                                                              
ሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር (SSN) መግለጫ (ማረጋገጫ) ቅጽ 
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር
• የወላጅ ፈቃድ ማረጋገጫ (እድሜያቸው 16 ወይም 17 አመት ከሆነ)

 

የመሸጋገሪያ የመንጃ ፈቃድ  (እድሜ  16 ½ – 20 )  <<ወደላይ መመለስ>>

የሪል መታወቂያ የመሸጋገሪያ መንጃ ፈቃድ ማግኘት - እድሜዎ ከ21 አመት በታች መሆን አለቦት፣ የለማጅ ፈቃድ ሊኖሮት ይገባል፣ የጎዳና ላይ ችሎታን ፈተና ወስደው ያለፉ መሆን እና የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላት አለቦት።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንክ(ማገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ  
• ቢያንስ ለ 6 ወራት ምንም ነጥብ የሚያስይዙ ጥሰቶች የሌለበት ትክክል የሆነ (የሚሰራ) የለማጅ ፈቃድ
[ለመሸጋገሪያ ፈቃድ የብቁነት ማረጋገጫ ቅጽ] [Certification of Eligibility for Provisional License form]
• የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተናን ማለፍ
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር


ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግል የመሸጋገሪያ የመንጃ ፈቃድ ማግኘት – እድሜዎ ከ 21 አመት በታች መሆን አለበት፣ የዲሲ ለተወሰኑ ጎዳዮች የሚያገለግል የለማጅ ፈቃድ ሊኖሮ ይገባል፣ የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተናን ወስደው ያለፉ መሆን አለቦት እና የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላት አለቦት።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(መገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

• ቢያንስ ለ 6 ወራት ነጥብ የሚያስይዙ ጥሰቶች የሌለበት የዲሲ ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግሉ የለማጅ ፈቃድ
[ለመሸጋገሪያ ፈቃድ የብቁነት ማረጋገጫ ቅጽ] [Certification of Eligibility for Provisional License form]
• የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተናን ማለፍ
• ለዲሲ ወይም ሌላ ባለስልጣን (ክልል) ምንም አይነት ያልተከፈለ እዳ አለመኖር

 

የመንጃ ያልሆነ- የመታወቂያ ወረቀት  <<ወደላይ መመለስ>>

የሪል መታወቂያ (REAL ID) የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ ካርድ - እድሜዎ ቢያንስ 15 አመት መሆን አለበት እና ከዲሲ ወይም ከሌላ ባለስልጣን ክልል የሚሰራ የመንጃ ፈቃድ የሌሎት መሆን አለቦት።
መስፈርቶች
ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(መገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ

ለተወሰነ ጉዳዮች የሚያገለግል የመንጃ ያልሆነ መታወቂያ ወረቀት ማግነት - እድሜዎ ቢያንስ 15 አመት መሆን አለበት እና ከዲሲ ወይም ከሌላ ባለስልጣን ክልል የሚሰራ የመንጃ ፈቃድ የሌሎት መሆን አለቦት። ለተወሰነ ጉዳዮች የሚያገለግል የመንጃ ያልሆነ መታወቂያ ወረቀት ለማውጣት ቀጠሮ ማስያዝ አለቦት።

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንኮች(መገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የማንነት ማረጋገጫ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ
ዲሲ ውስጥ 6-ወራት እንደኖሩ ማረጋገጫ                                                        
ሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር (SSN) መግለጫ (ማረጋገጫ) ቅጽ

 

የማንነት ማረጋገጫ <<ወደላይ መመለስ>>

ሪል መታወቂያ (REAL ID) መንጃ ፈቃድ/የመታወቂያ ወረቀት – ከታች ካለው ዝርዝር መሀል አንዱን ያቅርቡ:

• የዩ.ኤስ. የልደት ምስክርነት ወረቀት(በርዝ ሰርተፍኬት) ወይም የበርዝ ሰርተፍኬት ካርድ
• ቀኑ ያልተቃጠለ ሪል መታወቂያ (REAL ID) የመንጃ ፈቃድ፣ የለማጅ ፈቃድ፣ የመታወቂያ ወረቀት
• ቀኑ ያልተቃጠለ የዩ.ኤስ. ፓስፖርት
• ቀኑ ያልተቃጠለ የዩ.ኤስ. የጦር ሀይል የመታወቅያ ወረቀት
• የዜግነት(ናቹራላይዜይሽን) ሰርተፍኬት
• የዩ.ኤስ. ዜግነት ሰርተርኬት
• ውጭ አገር መወለድን የሚያሳይ የኮንስላር ሪፖርት
• ከሲሶሳ (CSOSA) ወይም  ዲሲ ዲኦሲ (DC DOC) ደብዳቤ (ለመታወቂያ ወረቀት ብቻ)
• ቪዛ እና የቆይታን ግዜን የሚያሳይ I-94  ያለው ቀኑ ያልተቃጠለ ፓስፖርት
• ቪዛ (A እና G) ፣ I-94፣ ያለው ቀኑ ያልተቃጠ ፓስፖርት እና የዩ.ኤስ. ስቴት ዲፓርትመንት ደብዳቤ
• ቪዛ (F) ያለው፣ I-94  እና I-20 ያለው ቀኑ ያልተቃጠለ ፓስፖርት
• ቪዛ (J)፣ I-94 እና DS-2019 ያለው ቀኑ ያልተቃጠለ ፓስፖርት
• ቀኑ ያልተቃጠለ የስራ ፈቃድ ካርድ
• ቀኑ ያልተቃጠለ ቋሚ የመኖሪያ ካርድ
• I-94 ማህተም ያለበት አሳይሊ እና የአሳይለም ፈቃድ የተሰጠበት ደብዳቤ
• I-94 ማህተም ያለበት ሪፊጂ (Refugee)

የጉብኝት ቪዛ ያላቸው የዩ.ኤስ. ዜጋ ያልሆኑ የዲሲ ሪል መታወቂያ (DC REAL ID) መንጃ ፈቃድ ወይም ዲሲ ሪል መታወቂያ ወረቀት ለማግኘት ብቁ አይደሉም። የዩ.ኤስ ዜጋ ያልሆኑ፣ የዩ.ኤስ.ሲ.አይ.ኤስ  የእርምጃ ማስታወሻ (USCIS Notice of Action)፣ ቅጽ  I-797፣ የስራ ፈቃድ፣ ቋሚ መኖሪያ ፈቃድ ማመልከቶን እንዳስገቡ የሚያሳይ ወይም የሁኔታ ማስተካከያ(አጀስትመንት) መኖሩን የሚያሳይ ወይም በህጋዊ መንገድ መቆየትን የሚፈቅድ በዩ.ኤስ.ሲ.አይ.ኤስ (USCIS) ወይም ዩ.ኤስ ዲፓርትመንት ኦፍ ስቴት የታተመ ቀኑ ያልተቃጠለ ማንኛውም የወረቀት ማስረጃ ካላቸው የዲሲ ሪል መታወቂያ (DC REAL ID) መንጃ ፈቃድ ወይም ዲሲ ሪል የመታወቂያ ወረቀት ለማግኘት ይችሉ ይሆናል።

ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግል መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ወረቀት  – ከታች ካለው መሀል አንዱን ያቅርቡ:

• ቀኑ ያልተቃጠለ ፓስፖርት
• የኮንሱላር ካርድ (ሜክሲኮ፣  ጉዋተማላ፣ ወይም ኢኩዋዶር)
• የዩናይትድ ስቴትስ የትውልድ ምስክር ወረቀት(በርዝ ሰርተፍኬት) ወይም በስቴት ቫይታል ኦፍስ (State Office of Vital Statistics) የተመዘገበ በርዝ ሰርተፍኬሽን ካርድ 
• ከሲስሶሳ (CSOSA) ወይም  ዲሲ ዲኦሲ (DC DOC) ደብዳቤ (ለመታወቂያ ወረቀት ብቻ)

ወይም

ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግል መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ወረቀት  – ከታች ካለው መሀል ሁለቱን ያቅርቡ:

• የውጭ አገር የትውልድ ምስክር ወረቀት (ዋናው (ኦሪጅናል))
• የውጭ አገር የመንጃ ፈቃድ ወይም የመታወቂያ ወረቀት
• ቀኑ ያልተቃጠለ የዩ.ኤስ. የጦር ሀይል የመታወቅያ ወረቀት
• የተረጋገጠ(ሰርቲፋይድ) የትምህርት ማስረጃ(ሪከርድ)

በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያልሆነ ዋና ማስረጃ ወረቀት ከውጭ አገር ከሆነ ያሎት፣ የእንግሊዘኛውን ትርጉም ከኢምባሲዎ ወይም ማረጋገጫ ካለው (ሰርቲፋይድ ከሆነ) አስተርጓሚ ማያያዝ አለቦት። የኢምባሲው ትርጉም ይፋ(ኦፊሻል) በሆነ ሌተር ሄድ ባለው መሆን አለበት። የተረጋገጠ (ሰርቲፋይድ የሆነ) የተርጓሚው ግልባጭ(ኮፒ) የማረጋገጫ ማህተም ሊኖረው ይገባል።

 

የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ <<ወደላይ መመለስ>>

የሪል መታወቂያ መንጃ ፈቃድ/መታወቂያ ወረቀት (REAL ID DL/ID) - ከታች ካለው መሀል አንዱን ያቅርቡ:

• ሶሻል ሴኪሪቲ ካርድ
• የሶሻል ሴኪሪቱ አስተዳደር ማረጋገጫ ህትመት(ፕሪንት የተደረገ)
• ባለፈው 12 ወራት ውስጥ የታተመ የክፍያ ወረቀት(ስቴትመንት)
• ባለፈው 12 ወራት ውስጥ የታተመ W-2 ወረቀት(ስቴትመንት)
• ባለፈው 12 ወራት ውስጥ የታተመ 1099 ቅጽ

ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግል የመንጃ ፈቃድ/መታወቂያ ወረቀት – እታች ያለውን ቅጽ ያቅርቡ:

የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ያልተመደበሎት መሆኑን፣ የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ተመድቦሎት ኖሮ ነገር ግን ማመልከቻውን ባቀረቡበት ግዜ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ህጋዊ ሆነው እንደቆዩ ሊያረጋግጡ እንደማይችሉ፣ ወይም የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ለመቀበል ብቁ እንዳልሆኑ ለማረጋገጥ የሶሳል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ ቅጽ ይሙሉ።

 

የነዋሪነት ማረጋጫ <<ወደላይ መመለስ>>

ከታች የተዘረዘሩትን ሁለት ማስረጃ ወረቀት ያቅርቡ:

• ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ የታተመ የመጠቀሚያ(ዩቲሊቲ) ክፍያ
• ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ የታተመ የስልክ ክፍያ
• የባለቤትነት ደብተር (Deed) ወይም የስምምነት ወረቀት
• ቀኑ ያልተቃጠለ ሊዝ ወይም የኪራይ ስምምነት
• ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የታተመ  የዲሲ የንብረት ግብር መክፈያ(ቢል)
• ቀኑ ያልተቃጠለ የቤት ባለቤት ወይም ያከራይ ኢንሹራንስ ፖሊሲ
• ከሲሶሳ (CSOSA) ወይም  ዲሲ ዲኦሲ (DC DOC) ፎቶግርፍ ያለው ደብዳቤ (ለመታወቂያ ወረቀት ብቻ)
• ዲሲ ዲኤምቪ(DC DMV) የነዋሪነት ማረጋገጫ ቅጽ
• ባለፈው 60 ቀናት ውስጥ የታተመ የባንክ ደብተር ዝርዝር (ስቴትመንት)
• ባለፈው 60 ቀናት ውስጥ ከፌዴራል፣ ከክልል (ስቴት)፣ ወይም ከሎካል መንግስት ኤጅንሲ፣ ከዲሲ ዲኤምቪ ውጪ ከሆነ፣  የደረሶት የፈርስት ክላስ ወይም ፕራዮሪቲ ሜል  (ፖስታ) ፣ ፖስታውን እና ውስጡ ተደርጎ የተላከውን

ማካተት አለበት 

ለተወሰነ ጉዳዮች ማረጋገጫ፣ የዲሲ የ6-ወር ነዋሪነት ማረጋገጫ

ከታች የተዘረዘሩትን ሁለት ማስረጃ ወረቀት ያቅርቡ (ቀኖቹ ቢያንስ ከማመልከቻው ቀን ስድስት ወር በፉት የሆነ):

• የመጠቀሚያ የክፍያ ወረቀት( ዩቲሊቲ ቢል)
• የስልክ ክፍያ(ቢል)
• የባለቤትነት ደብተር (Deed) ወይም የስምምነት ወረቀት
• ቀኑ ያልተቃጠለ ሊዝ ወይም የኪራይ ስምምነት
• የዲሲ የንብረት ግብር ክፍያ ወረቀት(ቢል)
• ቀኑ ያልተቃጠለ የቤት ባለቤት ወይም ያከራይ ኢንሹራንስ ፖሊሲ
• ከሲሶሳ (CSOSA) ወይም  ዲሲ ዲኦሲ (DC DOC) ፎቶግርፍ ያለው ደብዳቤ (ለመታወቂያ ወረቀት ብቻ)
• ዲሲ ዲኤምቪ(DC DMV) የነዋሪነት ማረጋገጫ ቅጽ
• የባንክ ደብተር ዝርዝር (ስቴትመንት)
• ከፌዴራል፣  ከክልል (ስቴት)፣ ወይም ሎካል መንግስት ኤጅንሲ፣ ከዲሲ ዲኤምቪ ውጪ ከሆነ፣ የደረሶት ፈርስት ክላስ ወይም ፕራዮሪቲ ሜል  (ፖስታ) ፣ ፖስታውን እና ውስጡ ተደርጎ የተላከውን ማካተት አለበት

 

የመንዳት ችሎታ ማረጋገጫ  <<ወደላይ መመለስ>>

እታች እንደተዘረዘሩት ቢያንስ አንድ ዋና የማስረጃ ወረቀት ማቅረብ አለቦት:

• ከስቴት ውጪ የሆነ የመንጃ ፈቃድ፣ ከ 90 ቀን በላይ ተቃጥሎ(ኤክስፓየር አርጎ) ያልቆት
• ከስቴት ውጪ የሆነ የተረጋገጠ(ሰርቲፋይድ) የመንዳት መዝገብ  (ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ የታተመ)፣ ከ 90 ቀን በላይ ተቃጥሎ(ኤክስፓየር አርጎ) ያልቆት
• ትክክል(የሚሰራ) ከሀገር ውጪ የሆነ የመንጃ ፈቃድ

 

የአድራሻ ለውጥ  <<ወደላይ መመለስ>>

የዲሲ ነዋሪዎች የአድራሻ ለውጥን በ 60 ቀናት ውስጥ ማስቀየር አለባቸው። የሪል መታወቂያ መንጃ ፈቃድ/መታወቂያ ወረቀት ወይም ለተወሰነ ጉዳይ የሚያገለግል መንጃ ፈቃድ/መታወቂያ ወረቀት ካሎት፣ አድራሻዎትን በኢንተርኔት (ኦን ላይን) መቀየር ወይም አስፈላጊ የሆኑትን የነዋሪነት ማረጋገጫ ማስረጃ ወረቀቶች በፖስታ ለዲኤምቪ (DMV) መላክ ይችላሉ። ሌላ በዲኤምቪ የሚያስፈጽሙት ነገር ከሌለ፣ የአድራሻ መቀየሪያ ክፍያም አለው።

አድራሻ ለመቀየር የዲኤምቪ የአገልግሎት ስፍራ በአካል ከሄዱ፣ ወይም የሪል መታወቂያ መንጃ ፈቃድ/መታወቂያ ወረቀት ወይም ለተወሰነ ጉዳይ የሚያገለግል መንጃ ፈቃድ/መታወቂያ ወረቀት ከሌሎት በአካል ሲመጡ ማምጣት ያለቦትን በአካል የመታወቂያ ወረቀት መተኪያ ተጨማሪ የሚያስፈልጉትን ማስረጃ ወረቀቶችን ማየት አለቦት። 

መስፈርቶች

ከእያንዳንዱ ክፍል ማምጣት ያለቦትን  አስፈላጊ ማስረጃ ወረቀቶች ዝርዝር ለማየት እታች ያለውን ሊንክ(መገናኛ) በሙሉ ይጫኑ እናም ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል ይዘጋጁ።

የሪል መታወቂያ (REAL ID) የማንነት ማረጋገጫ
የሪል መታወቂያ (REAL ID) የሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር ማረጋገጫ    
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ

ወይም

ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግል (Limited Purpose) የማንነት ማረጋገጫ
ሶሻል ሴኪሪቲ ቁጥር (SSN) መግለጫ(ማረጋገጫ) ቅጽ
የዲሲ ነዋሪነት ማረጋገጫ

 

የነጂ መዝገብ (ሪከርድ) <<ወደላይ መመለስ>>

ማረጋገጫ የሌለው(ሰርትፋይድ ያልሆነ) የነጂ መዝገቦን (ሪከርድ) በኢንተርኔት(ኦንላይን) መጠየቅ ይችላሉ። ማረጋገጫ ያለው(ሰርትፋይድ የሆነ) የነጂ መዝገቦን በፖስታ ወይም በአካል ወደ ዲኤምቪ የአገልግሎት ስፍራ በመሄድ እና ተገቢውን ክፍያ በመክፈል ሊጠይቁ ይችላሉ።
በፖስታ የነጂ መዝገቦን ግልባጭ ለመጠየቅ ወደሚከተለው ደብዳቤ ይላኩ:
DMV
Attn: Driver Records
PO Box 90120
Washington, DC 20090

 

የሞተር ሳይክል  ፈቃድ(ኢንዶርስመንት) <<ወደላይ መመለስ>>

ዲሲ ውስጥ ሞተርሳይክል ለማንቀሳቀስ ትክክል የሆነ (የሚሰራ) የመንጃ ፈቃድ ከሞተርሳይክል (M) ፈቃድ (ኢንዶርስመንት) ጋር ሊኖሮት ይገባል።

መስፈርቶች

• እድሜ 18 አመት
• ቀኑ ያልተቃጠለ የዲሲ የመንጃ ፈቃድ
• የዲሲየሞተርሳይክል የእውቀት ፈተና ማለፍ
• የዲሲ ዲኤምቪን የሞተርሳይክል ችሎታ ማሳያ ፈተናን ማለፍ ወይም የሞተር ሳይክል ማሳያ ትምህርት ማጠናቀቅን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት፣ ባለፉት 6 ወራት፣ በዲሲ፣ ሜሪላንድ ወይም ቨርጂንያ የጸደቀ።

 

የህክምና መስፈርቶች  <<ወደላይ መመለስ>>

የሞተር ተሽከርካሪን ለማንቀሳቀስ የሚያግዶት የጤና ሁኔታ ካለቦት፣ ግዚያዊ እንኳን ቢሆን፣ ከሀኪሞ የጤና እና/ወይም የአይን ሪፖርት ማምጣት አለቦት። 

 

የጉዳተኞች ታርጋ እና ማሳያ <<ወደላይ መመለስ>>

ዲኤምቪ ለተሽክረካሪዎ የጉዳተኞች ታርጋ  እና የማቆምያ(ፓርኪንግ) ማሳያ ይሰጣል።
 

የጉዳተኞች ማቆምያ ማሳያ ወይም ታርጋ ማመልከቻ በሀኪም መሞላት አለበት እና በፖስታ ወደ DC DMV, Medical Review Services, PO Box 90120, Washington, DC 20090 ወይም በፋክስ (202) 673-9908 ሊላክ፣ ወይም በአካል ወደ ማንኛውም ዲኤምቪ አገልግሎት ማእከል ሊወሰድ ይችላል።

የተሽከርካሪዎን ምዝገባ ላይ ተመስርቶ፣ የጉዳተኞች ታርጋን ለአንድ ወይም ሁለት አመት ለማግኘት ምርጫው አሎት።

ለጉዳተኞች የማቆምያ ማሳያ ወይም ታርጋ ምንም ክፍያ የለውም። የፕሌዠር ታግ(ታርጋ) ካሎት እና የጉዳተኞች ታግ(ታርጋ) የሚያወጡ ከሆነ፣ የታርጋ ማዘዋወሪያ ክፍያ አለው። 

 

የመንዳት ፈተናዎች (እውቀት፣ ችሎታዎች እና ሞተርሳይክል ፈተናዎች) <<ወደላይ መመለስ>>

የእውቀት ፈተና

የመንዳት የእውቀት መመዘኛ የትራፊክ ህግን፣ የመንገድ ምልክቶች፣ የመንዳት ደህንነት ደንቦች እውቀቶን ይፈትኖታል። በዲሲ ህግ መሰረት ተሽከርካሪን ለማንቀሳቀስ ዝግጁ መሆኖትን ይወስናል። ፈተናው በዲኤምቪ አገልግሎት ማእከሎች ይሰጣል እና በበርካታ ቋንቋዎች ይቀርባል። በኦድዮ የሚደገፉት ፈተናዎች ለማንበብ እርዳታ ለሚፈልጉትም ጭምር ይሰጣል። የዲሲ የመንዳት ማንዋልን ከኢንተርኔት (ኦን ላይን) ሊያገኙት ይችላሉ።

የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተና

የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተና በዲሲ ዲኤምቪ የቀጠሮ ሲስተም ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው፣ ወይም ሶስተኛ አካል የሆነ ፈታኝ በመጠቀም።

በፈተናዎ ቀን፣  ወደ ዲኤምቪ የጎዳና ላይ ፈተና መውሰጃ አገልግሎት ስፍራ ይሂዱ። የጎዳና ላይ ፈተናን በ 12 ወራት ውስጥ  6 ግዜ ከወደቁ፣  1ኛውን ፈተና ከወደቁበት አንስቶ እስከ  12  ወራት ድረስ 7ኛውን ፈተና መውሰድ አይፈቀድሎትም።

አስፈላጊ ነገሮች

ማድረግ ያለቦት:

• ቢያንስ ከቀጠሮው 15 ደቂቃ በፊት መድረስ
• እታች ያለውን የተሽከርካሪ መስፈርቶች የሚያሟላ ተሽከርካሪ ውስጥ ሆነው መምጣት
• ትክክል የሆነ(የሚሰራ) የለማጅ ፈቃዶን ማምጣት
• እድሜያቸው 21 አመት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ፈቃድ ያላቸው ነጂ ጋር አብሮት መሆን
• ትክክል የሆነ(የሚሰራ) ምዝገባ(ሬጅስትሬሽን) እና የኢንሹራንስ ማረጋገጫ  ያለው መኪና ማምጣት
• የደህንነት ቀበቶውን(ሲት ቤልት) ማድረግ
• እድሜዎ ከ21 አመት በታች ከሆነ፣ የ40- ሰአት [ለመሸጋገሪያ ፈቃድ የብቁነት ማረጋገጫ ቅጽ] [Certification of Eligibility for Provisional License form] ያምጡ፣

እባኮን ያስተውሉ: የለማጅ ፈቃድ ካሎት እና ፈቃድ ያለው ነጂ አብሮት ሳይኖር ወደ ጎዳና ፈተናው ቀጠሮ እራሶት ነድተው ከመጡ፣ ፈተናውን ለ 6 ወራት መውሰድ አይፈቀድሎትም። የጎዳና ላይ ችሎታ ፈተናን ከወደቁ፣ እንደገና ለመፈተን ብቁ ለመሆን 72 ሰአት መጠበቅ አለቦት።

የተሽከርካሪው መስፈርቶች

ፈተናን ለመውሰድ የሚጠቀሙበት ተሽከርካሪ ማሟላት ያለበት:

• ወቅታዊ የምዝገባ ካርድ መስኮት ላይ ከሚለጠፍ የምዝገባ ስቲከር ጋር ወይም ከታርጋው ጋር የተያያዘው የሚሰራ የሚቃጠልበትን ቀን የሚያሳይ ስቲከር።
• ተሽከርካሪውን የሚጠቁም እና የሚቃጠልበትን ቀን ያለበት፣ የሞተር ተሽከርካሪ ሀላፊነት(ሊያቢሊቲ) ኢንሹራንስ ካርድ/ፖሊሲ
• የሚሰራ ኢንስፔክሽን ስቲከር የሚያሳይ፣ ተገቢ ከሆነ። ኢንስፔክሽን መውደቃቸውን የሚያሳዩ ስቲከር ያላቸው ተሽከርካሪዎች ለጎዳና ላይ ፈተና ተቀባይነት የላቸውም።
• ከባምፐሩ ጋር በአግባቡ የተያያዘ የፉት እና የሃላ ታርጋን የሚያሳይ ( አግባብ ካለው)
• በደንብ የሚሰሩ የፍሬን መብራት፣ የመታጠፊያ ምልክት መብራቶች፣ ጥሩምባ(ክላክስ)፣ ወደላይ ሚወጣ እና  ወደታች የሚወርድ መስኮቶች፣ ከውስጥ እና ከውጭ መያዣ ያላቸው የሚሰሩ በሮች፣ የውስጥ ወደሃላ ማሳያ መስተዋት እና

በደንብ የተገጠሙ የውጭ ከጎን (ግራ/ቀኝ) ማሳያ መስታዋቶች፣ እና ከነጂው እና ከፉት ተሳፋሪው መቀመጫ መሃከል የሆነ የአደጋ ግዜ(ኢመርጀምሲ) የእጅ ፍሬን 

• ያልተከለለ ሰፊ እይታን የሚሰጥ እና የሃላውን ማሳያ መስታዋት ላይ ምንም ያልተንጠለጠለበት፣  ምንም መሰንጠቅ ወይም ፍንጥርጣሪ የሌለው የፊት መስታዋት(መስኮት)
• በጥሩ ሁኔታ ያሉ እና በአግባቡ የተነፉ ጎማዎች፣ መቀየሪያ(ዶናት) ጎማዎች ተቀባይነት የላቸውም።
• የኪራይ መኪናዎች ለጎዳና ላይ ፈተና የሚፈቀዱት፣ ፈተናውን የሚወስደው ሰው በኪራይ መኪና ውሉ ላይ በኪራዩ መኪና መንዳት እንደ ተፈቀደለት ነጂ ሆኖ ከተመዘገበ ብቻ ነው።
• በዳሽ ቦርዱ ላይ ምንም የሰርቪስ ወይም ማስጠንቀቂያ መብራት ያላበራ፣ ዝቅተኛ ነዳጅን ጨምሮ።

ማስታወሻ: ቀጠሮ የተያዘበትን የጎዳና ላይ ፈተና በሁለት የስራ ቀናት ውስጥ ሳይሰርዙት ለቆዩ፣ የመሰረዣ ክፍያ አለው።

የሞተር ሳይክል እውቀት ፈተና 

የዲሲ ዲኤምቪ ሞተር ሳይክል እውቀት ፈተናን ለመውሰድ፣ የዲኤምቪ አገልግሎት ማእከልን ጋር መሄድ ይችላሉ። የሞተርሳይክል የእውቀት ፈተናውን ካለፉ በሃላ፣ የዲሲ ሞተርሳይክል የለማጅ ፈቃድ ሊኖሮት ይገባል።

 

የግራድ (GRAD) ፕሮግራም <<ወደላይ መመለስ>>

የቀስ በቀስ አዋቂ ነጂነት ማሳደጊያ ፕሮግራም (Gradual Rearing of Adult Drivers (GRAD)) አዲስ ነጂዎችን (16-20 እዱሜ) ሙሉ የመንጃ ፈቃድ መብት ከማግኘታቸው በፉት ደህንነትን በጠበቀ መንገድ የመንዳት ልምድ እንዲያዳብሩ ይፈቅዳል።የትራፊክ ህግን ወይም የግራድ (GRAD) ፕሮግራም መስፈርቶችን ከጣሱ ቅጣት አለው።
እድሜያቸው 21 አመት ሲሆን ሁሉም የግራድ የግራድ (GRAD) ነጂዎች ከፕሮግራሙ ነጻ ይሆናሉ።
እድሜያቸው 16 ወይም 17 አመት የሆናቸው አመልካቾች፣ የወላጆቻቸው ወይም የህጋዊ ሞግዚቶቻቸው የዲሲ የመንጃ ፈቃድ ወይም የዲሲ መታወቂያ ወረቀት ግልባጭ (ፎቶ ኮፒ) እና ከሚከተሉት የማስረጃ ወረቀቶች አንዱ

ሊኖራቸው ይገባል:

• ከወላጅ ወይም ከህጋዊ ሞግዚት የወላጅ የፈቃድ ቅጽ
• የለማጅ ፈቃድ እንዲሰጥ ስምምነትን የሚሰጥ፣ ኖተራይዝድ የሆነ፣ ከወላጅ ወይም ህጋዊ ሞግዚት የተጻፈ ደብዳቤ

የግራድ (GRAD) የተፈቀዱ የመንጃ ሰአታት
የለማጅ ፈቃድ ሴፕቴምበር  ኦገስት
ሁሉም ቀን – 6 am – 9 pm

የመሸጋገሪያ ፈቃድ እና ሙሉ ፈቃድ እድሜ   16 እና 17 አመት ሴፕቴምበር - ጁን
እሁድ - ሀሙስ፣ 6 am – 10:59 pm
አርብ እና  ቅዳሜ፣ 6 am – 11:59 pm
ጁላይ እና ኦገስት
ሁሉም ቀን፣  6 am – 11:59 pm


አካል(ኦርጋን) እና ቲሹ ለጋሾች  <<ወደላይ መመለስ>>

የመንጃ ፈቃድ ወይም የመታወቂያ ወረቀት ሲያወጡ ወይም ሲያድሱ የአካል ወይም ቲሹ ለጋሽ ለመሆን መመዝገብ ይችላሉ። የበለጠ መረጃ በ http://www.donatelifedc.org/ ይገኛል።

 

አግባብ ያላቸው ክፍያዎች  <<ወደላይ መመለስ>>

ዲኤምቪ ጥሬ ገንዘብ(ካሽ)፣ ቼክ፣ መኒ ኦርደር፣ ዴቢት ካርድ ወይም ክሬዲት ካርድ ይቀበላል፣ ከሚከተሉት በስተቀር፡

1) ዲኤምቪ፣ ቪዛን (VISA) ፣ ማስተር ካርድን (MasterCard) እና ዲስካቨሪ (Discover) ክሬዲት ካርዶችን ይቀበላል። ዲኤምቪ አሜሪካን ኤክስፕረስን (American Express) አይቀበልም።
2) በጎዳና ላይ ፈተና/ ሲዲኤል ቢሮ ወይም ሲዲኤል የፈተና ቦታዎች (CDL Office or CDL Testing Facility) ካሽ አንቀበልም

 

የመንጃ ፈቃድ / የመታወቂያ አገልግሎቶች ክፍያ
የመንጃ ፈቃድ (አዲስ እና ማሳደስ) $44
የመሸጋገሪያ የመንጃ ፈቃድ $20
የለማጅ ፈቃድ $20
የእውቀት ፈተና $10
መታወቂያ ወረቀት (አዲስ እና ማሳደስ) $20
ለአረጋውያን መታወቂያ ወረቀት ( እድሜያቸው 65 +) ነጻ
ለቀድሞው አጥፉዎች (Ex-Offenders) መታወቂያ ወረቀት ነጻ
ቤት አልባ(ሆምለስ) ለሆኑ የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ ወረቀት ነጻ
የመንጃ ፈቃድ ግልባጭ (Duplicate) $20
የመታወቂያ ወረቀት ግልባጭ (Duplicate) $20
የለማጅ ፈቃድ ግልባጭ (Duplicate) $20
የግዚያዊ የመንጃ ፈቃድ እና የመታወቂያ ወረቀት $20
የመንጃን ፈቃድ እንደገና መልሶ ማግኘት (Reinstatement) $98
የጎዳና ላይ ፈተና $10
የጎዳና ላይ ፈተናን ለመሰረዝ $30
አድራሻ መቀየር $20
የነጂው መዝገብ(ሪኮርድ) 3 እስከ 5-አመት ታሪክ $7
የነጂው መዝገብ(ሪኮርድ) 10-አመት እና ሙሉ ታሪክ $13

 

ሌሎች የነጂ አገልግሎቶች መረጃዎች  <<ወደላይ መመለስ>>

ለሌላ ለማንኛውም የነጅዎች አገልግሎት መረጃዎች፣ እንደ ፈቃድ መታገድ፣ መሻር ወዘተ ለመሳሰሉ እርዳታ ለማግኘት በ 311 ወይም 202-737-4404 ያግኙን።
የነጅዎች አገልግሎት በርካታ የአገልግሎት ሰጪ ማእከሎት አሉት፣ እታች እንደተጠቀሱት። የሁሉም ስፍራዎች የስራ ቀናት እና ሰአታት ማክሰኞ – ቅዳሜ፣ 8:15am – 4:00pm ነው።

ጆርጅታውን የአገልግሎት ማእከል (ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 29፣ 2014 የሚከፈት)
(Georgetown Service Center)
3270 M Street, NW
Lower Level
Washington, DC  20007

ሮድ አይላንድ የአገልግሎት ማእክል
(Rhode Island Service Center)
2350 Washington Place, NE
Suite 112N
Washington, DC 20018

ሳውዝዌስት የአገልግሎት ማእክል
(Southwest Service Center)
95 M Street, SW
Washington, DC  20024

ብሬንትዉድ ሲዲኤል እና የጎዳና ላይ ፈተና ቢሮ
(Deanwood CDL & Road Test Office)
1421 Kenilworth Avenue, NE
Washington, DC 20019
በተለያዩ የአገልግሎት ማእከላት ያለውን የደንበኛ ብዛት ለማየት እዚህ ጋር ይጫኑ 

 

የነጅዎች አገልግሎት ቅጾች እና የኦንላይን  ማስፈጸሚያዎች(ግብይቶች) <<ወደላይ መመለስ>>

 

የታረመበት:  ማርች 24፣ 2014