Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dmv

Department of Motor Vehicles
 

DC Agency Top Menu

-DC DMV will no longer prevent DC residents from applying for a new or renewed driver license because of failing to meet the requirements of the Clean Hands Law.

-A +A
Bookmark and Share

Amharic Vehicle Services

የተሽከርካሪ አገልግሎቶች

ከዚህ በታች ዲኤምቪ የሚሰጣቸውን የተሽከርካሪ አገልግሎቶች አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ ያገኛሉ:

የተሽከርካሪ ምዝገባ
የተሽከርካሪ ምርመራ
የተሽከርካሪ ባለቤትነት ሰነዶች (ታይትል)
የተሽከርካሪ ታርጋ 
የማቆሚያ ፈቃድ/ የቅይይር (የሬሲፕሮሲቲ) ስቲከሮች
የአካል ጉዳተኛ ታርጋዎች እና የማሳያ ምልክት ካርድ
የተሽከርካሪ አገልግሎቶች መጠየቂያ ቅፆች እና ኦንላይን የሚከናወኑ ተግባራት(በኢንተርኔት)

የተሽከርካሪ ምዝገባ << back to top >>

የዲሲ ሕግ በዲስትሪክቱ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በሙሉ፣ ባለቤቱ በዲኤምቪ የተሰጠ የቅይይር (የሬሲፕሮሲቲ) ስቲከር ያለውን ሳይጨምር፣ በዲስትሪክቱ እንዲመዘገቡ ያዛል። በነዋሪነት ከሌላ ቦታ ወደ ዲስትሪክቱ የሚመጡ የተሽከርካሪ ባለቤቶች ዲሲ ከገቡበት ቀን አንስቶ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የዲሲ ምዝገባ ማግኘት ይኖርባቸዋል። ለመመዝገብ ብቁ የሚሆኑት ዲሲ ዋና መኖሪያቸው የሆኑ ግለሰቦች እና የንግድ ድርጅቶች ብቻ ናቸው። ተሽከርካሪዎቹ ለመመዝገብ የዲሲ የባለቤትነት ሰነድ(ታይትል) እና የዲሲ ወቅታዊ የመድን ዋስትና(ኢንሹራንስ) ሊኖራቸው ይገባል።

የአዲስ ተሽከርካሪ ምዝገባ-አጠቃላይ መረጃ

• በዲሲ የተመዘገቡተሽከርካሪዎች በሙሉ ምርመራውን ማለፍ የሚገባቸው ሲሆን ይህም የምንጭ ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት (Certificate of Origin) (ማለትም የአዲስ ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ሰነድ) ያላቸውን አዲስ ተሽከርካሪዎችን አይጨምርም።  ይህም ሆኖ እነዚህ አዲስ ተሽከርካሪዎች በዲኤምቪ የተሰጠ የምርመራ ስቲከር መለጠፍ ይኖርባቸዋል።
• በዲኤምቪ የአገልግሎት ማዕከል ምዝገባ እና የማረጋገጫ ሰነድ ለማግኘት የዲሲ የመድን ዋስትና ማረጋገጫ(ኢንሹራንስ) ማቅረብ፣ አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ እና አግባብነት ያላቸውን ክፍያዎች መክፈል ይገባል።

              • የዲሲ የመንጃ ፈቃድ ወይም የመታወቂያ ወረቀት ማረጋገጫ
                        • የተሽከርካሪን ባለቤትነት ለማረጋገጥ ወይም ለማስመዝገብ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ከቀዳሚ ምንጭ የተገኘ አንድ ሰነድ በማቅረብ የዲሲ የመንጃ ፈቃድን ወይም የመታወቂያ ወረቀትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል;;

                         • ቀዳሚ የማረጋገጫ ምንጭ (አንድ የግድ አስፈላጊ ነው)- ዋናው(ኦርጅናል) መሆን አለበት

                                     • ቀኑ ያልተቃጠለ የዲሲ የመንጃ ፈቃድ
                                     • ቀኑ ያልተቃጠለ የዲሲ የለማጅ ፈቃድ
                                     • ቀኑ ያልተቃጠለ የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ ወረቀት

• ተሽከርካሪ ሲመዘገብ ቀናቸው ያልተቃጠለ ታርጋዎች ከሌሎች ተሽከርካሪዎች ማስተላለፍ ይቻላል።
• አንድ ተሽከርካሪ ሲመዘገብ ተሽከርካሪውን የሚያስመዘግበው ግለሰብ ስም በባለቤትነት ሰነዱ(ታይትሉ) ላይ መጠቀስ አለበት። የባለቤትነት ዝውውር ሲካሄድ የባለቤትነት ማረጋገጫው ወደአዲሱ ባለቤት(ቶች) መዘዋወሩ በፊርማ መረጋገጥ የሚኖርበት ሲሆን ከባለቤትነት ማረጋገጫው እና ምዝገባው በፊት በነበሩ የመያዣ(ሊን)/የሊዝ የሰነድ ልውውጦች ላይ ሁሉም ባለቤቶች መዘርዘር ይኖርባቸዋል።

• ከአንድ በላይ ባለቤት ያለው ተሽከርካሪ ሲመዘገብ ቢያንስ ከባለቤቶቹ አንዱ የሚሰራ የዲሲ የመንጃ ፈቃድ ወይም የመታወቂያ ወረቀት ሊኖረው ይገባል;;

አንድ ተሽከርካሪ፡

• የሚሰራ ታርጋ ካለው በቀጥታ ወደ ምርመራ ሊወሰድ ይችላል።ተሽከርካሪው ምርመራውን ሲያልፍ በዲኤምቪ የአገልግሎት ማዕከል ሊመዘገብ ይችላል።
• የሚሰራ የዲሲ የምርመራ ማረጋገጫ ስቲከር ያለው ከሆነ እንደገና መመርመር ሳያስፈልገው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊወጣበት እና ሊመዘገብ ይችላል። ቀኑ የተቃጠለ የምርመራ ማረጋገጫ ስቲከር ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከመመዝገባቸው በፊት ምርመራ ማለፍ ይኖርባቸዋል::
• ቀኑ የተቃጠለ ታርጋ ካለው፣ ባለቤቱ የተሽከርካሪ ምዝገባው ለ5 ቀናት ያህል እንዲራዘም ለአንድ ጊዜ ብቻ ማመልከት ይችላሉ። ይህ ተጨማሪ ጊዜ የሚሰጠው ለተሽከርካሪ ምርመራ ነው። ይህን የጊዜ መራዘም ለማግኘት የሚከተለውን ያቅርቡ:

            • የተሽከርካሪ ምዝገባ
            • የዲሲ የመንጃ ፈቃድ ወይም የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ ካርድ
            • የሚሰራ የመድን ዋስትና(የኢንሹራንስ) ማረጋገጫ

• ቀኑ የተቃጠለ የዲሲ ያልሆነ ታርጋ ካለው እና ባለቤቱ በራሱ/በራሧ ስም ወይም በሊዝ/የመያዣ ባለቤት(ሊን ሆልደር) ስም የባለቤትነት ማረጋገጫ ካለው ባለቤቱ ተሽከርካሪውን ለማስመርመር የሚያስችለውን ጊዜያዊ የዲሲ ምዝገባ ሊያገኝ ይችላል።
• ሊዝ ተደርጎ ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫውን/ምዝገባውን ከማካሄድ በፊት የባለቤትነት ሰነድ መጠየቂያ ለሊዝ ሰጪው ኩባንያው መቅረብ እና ዋናውን(ኦርጅናል) የባለቤትነት ማረጋገጫውን መቀበል ያስፈልጋል። ተሽከርካሪውን ለማስመዝገብ ከሚያስፈልጉት ሰነዶች በተጨማሪ የተፈረመ የሊዝ ውል አስፈላጊ ነው።
• በመያዣነት ተሰጥቶ ከሆነ(ሊን ካለው) ለመያዣው ባለቤት የባለቤትነት ማረጋገጫ መጠየቂያ መቅረብ ይኖርበታል። የባለቤትነት ማረጋገጫው ለዲኤምቪ ሲቀርብ ተሽከርካሪው ሊመዘገብ ይችላል። የእኛ የኦንላይን የስቴት ውጪ ታይትል ያለበትን ሁኔታ የባለቤትነት ማረጋገጫውን መረከባችንን ያረጋግጣል።
• በዲሲ ነዋሪ አሁን የተገዛ ያገለገለ(አሮጌ) ተሽከርካሪ ከሆነ ባለቤቱ ተሽከርካሪውን ለማስመርመር የሚያስችለውን ጊዜያዊ ምዝገባ ሊያገኝ ይችላል።
• የተሽክርካሪው ባለቤት በመሞታቸው ምክንያት የተገኘ ከሆነ ለተጨማሪ መረጃ በ311 ወይም በ202-737-4404 ያግኙን።
• ባለቤቱ ተሽከርካሪውን በዲስትሪክቱ ውስጥ በተመዘገበ የንግድ ድርጅት ስም ለማስመዝገብ የሚፈልግ ከሆነ መሰረታዊው የንግድ ፈቃድ ከምዝገባ ማመልከቻው እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

የተሽከርካሪ ምዝገባ እድሳት

የተሽከርካሪዎ ምዝገባ ጊዜ ከማለፉ 60 ቀናት በፊት የዕድሳት ማስታወቂያ በፖስታ ወይም በኢሜል ይደርስዎታል;; ባለቀ ጊዜ(ሊያበቃ ሲል) ለተደረገ ኦንላይን ዕድሳት የምዝገባ ስቲከሮ በፖስታ እስከሚደርስ ድረስ ዲኤምቪ ለ45 ቀናት ያህል የሚያገለግል ጊዜያዊ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ይሰጣል። የተሽከርካሪ ምዝገባን ለማሳደስ የሚሰራ የዲሲ የተሽከርካሪ ምርመራ(ኢንስፔክሽን) ያስፈልጋል።

የተሽከርካሪ ምዝገባ ዕድሳት ማካሄድ የሚቻለው ኦንላይን ወይም በደብዳቤ ብቻ ነው። ዕድሳትን በዲኤምቪ የአገልግሎት ማዕከል በኣካል በመገኘት ማከናወን ኣይቻልም።

ኦንላይን(በኢንተርኔት) የምዝገባ እና የነዋሪ የማቆሚያ(ፓርኪንግ) ዕድሳት

ኦንላይን ለማሳደስ የሚያበቁ መስፈርቶችን ካሟሉ የተሽክርካሪዎን ምዝገባ በኢንተርኔት(ኦንላይን) ማሳደስ ይችላሉ።

የተሽከርካሪዎ ምዝገባ ጊዜው አልፎበት ከሆነ የኦንላይን የምዝገባ የምስክር ወረቀትዎን በተሽከርካሪዎ ዳሽቦርድ ላይ በመለጠፍ መጠቀም ይችላሉ። ይህ የምስክር ወረቀት የሚያገለግለው ዕድሳቱ ከተከናወነበት ዕለት አንስቶ ለ45 ቀናት ብቻ ነው።

ማስታወሻ: አሁን ያለዎትን የምዝገባ ስቲከር በፊት ለፊት መስተዋቱ (ዊንድሺልዱ) ላይ እንዳለ ማቆየት እና ጊዜያዊ የምዝገባ የምስክር ወረቀቱን በዳሽቦርዱ ላይ ማኖር ይገባዎታል። የነዋሪ የማቆሚያ ፈቃድ (RPP) ለማግኘት ብቁ ከሆኑ የምዝገባ ዕድሳቱን በሚያከናውኑበት ሂደት ይህንን ለማካተት ይህንኑ የሚመለከት ሳጥን ላይ ምልክት እንዲያደርጉ የኦንላይን ሂደቱ ያስችልዎታል። ከአንድ በላይ የምዝገባ ስቲከር ከለጠፉ ለቅጣት (ለትኬት) ሊዳረጉ ይችላሉ።

የኦንላይን የተሽከርካሪ ምዝገባውን ባጠናቀቁ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ዲኤምቪ የተሽከርካሪ የምዝገባ ካርድዎን እና መስኮት ላይ የሚለጠፍ ስቲከር በፖስታ ይልክልዎታል። በተጨማሪም፣ ብቁ ከሆኑ እና እንዲሰጥዎ ከጠየቁ የነዋሪ የማቆሚያ ፈቃድዎን  (RPP)  ያገኛሉ። የምዝገባ ስቲከርዎን በ10 ቀናት ውስጥ ካላገኙ ወደ ከተማው የስልክ ማእከል በ311 ይደውሉ።

ማስታወሻ: አንድ ግለሰብ በተሽከርካሪ ምዝገባ ዕድሳት ወቅት የአድራሻ ለውጥ የሚያደርግ ከሆነ የአድራሻ ለውጡ ተፈጻሚ የሚሆነው የቀዳሚነት ባለቤትነት ላለው ግለሰብ ብቻ ነው።

ምትክ የተሽከርካሪ ምዝገባ ስለማግኘት

ምትክ የምዝገባ ካርድ ለማግኘት የሚሰራ የማንነት ማረጋገጫን ማቅረብ እና አስፈላጊ ክፍያዎችን መክፈል የግድ ነው።

መንገዶች;

በኢንተርኔት(ኦንላይን)
• በኣካል

ማስታወሻ: አንድ ግለሰብ የሚጠይቀው የስም ለውጥ ከሆነ ግለሰቡ ይህንን በኣካል በመቅረብ ብቻ ማከናወን እና ለስም ለውጡ አስረጅ የሆኑ ደጋፊ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርበታል/ባታል;;

የአሽከካሪ የመድን ዋስትና(ኢንሹራንስ) ግዴታዎች

የግዴታ/ ያለ-ጥፋት የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ህግ (Compulsory/No-Fault Motor Vehicle Insurance Act) በዲሲ ውስጥ ለምዝገባ ወይም ቅይይር (ለሬሲፕሮሲቲ) ስቲከር የሚያመለክት ሰው የሚሰራ የዲሲ የተሽከርካሪ መድን ዋስትና (ኢንሹራንስ) እንዲኖረው ያስገድዳል። የመድን ዋስትናው (ኢንሹራንሱ) ተሽከርካሪው ተመዝግቦ እስከቆየበት ጊዜ ድረስ የጸና ሊሆን ይገባል። በመድን ዋስትና (ኢንሹራንሱ) የሚከሰቱ ክፍተቶች ለቅጣት ይዳርጋሉ። የተሽከርካሪ ታርጋዎች ለዲኤምቪ ተመላሽ ከመሆናቸው በፊት የመድን ዋስትናን (ኢንሹራንሱን) አይሰርዙ።
ቢያንስ የግድ ሊኖሩ የሚገባቸው የመድን ሃላፊነት(ኢንሹራንስ) ሽፋን ግዴታዎች:

 

ሽፋን የመጨረሻ ትንሹ መጠን
የንብረት ጉዳት ሃላፊነት $10,000
የሶስተኛ ወገን ሃላፊነት $25,000 በግለሰብ እና $50,000 በአደጋ

ዋስትና የሌለው ባለሞተር የኣካል ጉዳት
$25,000 በግለሰብ እና $50,000 በአደጋ
ዋስትና የሌለው ባለሞተር የንብረት ጉዳት $5,000 ሆኖ $200 ተቀናሽ(ዲዳክታብል) ሊኖረው የሚችል

 
በዲሲ በተመዘገበ ተሽከርካሪ ላይ ቀጣይነት ያለው የሚሰራ የመድን ዋስትና(ኢንሹራንሰ) አለመኖር የምዝገባ ታርጋ/የቅይይር (የሬሲፕሮሲቲ) ስቲከር ዕገዳን ያስከትላል።አንድ ግለሰብ የመድን ዋስትና ክፍተት ላለበት ለመጀመርያዎቹ ከ1 እስከ 30 ቀናት የ $150 ቅጣት ከመጀመርያዎቹ 30 ቀናት በኋላ ላሉት እያንዳንዱ ቀን $7፣ ጣሪያው  $2500 ሆኖ ቅጣት ይጣልበታል። የመድን ዋስትና ክፍተት ቅጣት ክፍያ በማናቸውም የዲኤምቪ የአግልግሎት ማዕከል ሊፈጸም ይችላል።

አደጋ በተፈጠረ ወቅት እባክዎ ለመድን ዋስትና (ኢንሹራንስ) ኩባንያው ያሳውቁ፤ እንዲሁም አደጋውን በሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት  ያስመዝግቡ። አደጋን ለዲኤምቪ ኣያሳውቁ።

የመድን ዋስትና(ኢንሹራንስ) ማረጋገጫ

የመድን ዋስትና ሰጪውን ኩባንያ ስም፣ የፖሊሲውን ቁጥር፣ የመድን ዋስትና የተገባለትን ሰው ስም እና የመድን ዋስትናው ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ ዝርዝር ያለበት ከመድን ዋስትና ኩባንያው የተሰጠ ሰነድ።

ከክልል (ስቴት) ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ምዝገባ (ROSA)

ለ30 ተከታታይ ቀናት በዲሲ ውስጥ የሚቆዩ አውቶሞቢሎች መመዝገብ እና በሕዝባዊ ሥፍራዎች በሚቆሙበት ወይም በሚሽከረከሩበት ወቅት የዲሲ የምርመራ ስቲከር እና ታርጋ ሊኖራቸው ይገባል። የሕዝባዊ ሥራዎች ዲፓርትመንት (Department of Public Works) የዲሲ የምዝገባ መሥፈርቶችን የማያሙዋሉ አውቶሞቢሎች በመኖርያ አካባቢዎች መኖራቸውን ይቆጣጠራል። አንድ አውቶሞቢል በሰላሳ ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከታየ የሚከተሉት እርምጃዎች ካልተወሰዱ በስተቀር አውቶሞቢሉ ለቅጣት ወረቀት (ሳይቴሽን) መታተም እና/ወይም በመንግስት ይዞታ ለመደረግ (ኢንፓውንድመንት) ሊዳረግ እንደሚገባ የሚያሳውቅ ማስጠንቀቂያ ሊወጣበት ይችላል።

ተደጋጋሚ ጎብኝዎች (በተደጋጋሚ ለአጭር ጊዜ የሚደረጉ ጉብኝቶች) በማናቸውም የዲኤምቪ የአገልግሎት ማዕከል ቀርበው ሪፖርት ማድረግ እና የሚከተሉትን ሰነዶች በማቅረብ የዲሲ ነዋሪ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡

• የሌላ ስቴት የመንጃ ፈቃድ ወይም የመታወቂያ ካርድ
• ዋና(ኦርጅናል) የኪራይ/ባለቤትነት ወይም ሞርጌጅ ሰነድ
• ወቅታዊ የሆነ የመጠቀሚያ መክፈያ (ዩቲሊቲ ቢል) (ቀኑ በ60 ቀናት ውስጥ የሆነ)
• በጥያቄ ውስጥ ያለው የተሽከርካሪ የሚሰራ የምዝገባ ካርድ

ሁሉም ሰነዶች በተሽከርካሪው ሕጋዊ ባለቤት ስም የወጡና የእርሱን አድራሻ የሚያመለክቱ ሊሆኑ ይገባል።

በተጨማሪም፣ አስፈላጊ ሰነዶችን በሚከተለው አድራሻ መላክ ይችላሉ:  DC Department of Motor Vehicles, Attn: ROSA Exemption, PO Box 90120, Washington, DC 20090።  በፖስታ የሚልኩ ከሆነ የአንድ ዓመት የROSA ነጻ ደረሰኝዎ በ15 ቀናት ውስጥ ይላክልዎታል።

ማስታወሻ: የ ROSA ነጻ መሆን ከመሰጠቱ በፊት የማስጠንቀቂያ ማሳሰቢያ ወይም በዲሲ ባለመመዝገብ ምክንያት የቅጣት ቲኬት ሊሰጥ ይገባል። ለተሽከርካሪዎ የወጣውን ማስጠንቀቂያ ይዘው ይምጡ ወይም በፖስታ ይላኩ።

የዲሲ ታርጋ ሊያገኙ ባለመቻሎ ምክንያት ቲኬት አግኝተው ከሆነ ስለቲኬቱ ኦንላይን፣ በፖስታ በመላክ ወይም በአካል በመቅረብ ሊከራከሩ ይችላሉ። ለROSA የነጻ ሁኔታ የተዘረዘሩትን አንድአይነት ሰነዶች ማቅረብ ይኖርብዎታል።

ከአንድ ዓመት ነጻነት በሃላ ሌላ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠዎ ከላይ የተገለጸውን ነፃ የመሆን ሂደት በድጋሚ ሊያከናውኑ ይችላሉ።

ማስታወሻ:  የ ROSA ነጻ ሰነድ ማለት የማቆሚያ ፈቃድ አይደለም፤ አንድን ተሽከርካሪ ከዲሲ የማቆሚያ ሕግጋት ነጻ አያደርግም። በተመሳሳይ መልኩ የጎብኝ የማቆሚያ ፈቃድ ከROSA ፕሮግራም ጋር አይገናኝም፣ እናም የጎብኝ የማቆሚያ ፈቃድ አንድን ተሽከርካሪ የRPP የጊዜ ወሰን ለመጣስ እና ከROSA ግዴታዎች ነጻ ለማድረግ አይችልም።

የተሽከርካሪ ምርመራ  << back to top >>

የዲሲ ነዋሪዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን ከማስመዘገባቸው በፊት የማስመርመር ግዴታ አለባቸው። የተጓዥ ተሽከርካሪዎች (passenger vehicles) ለሁለት ዓመት ሚያገለግል የጭስ (emission) ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን የንግድ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ለአንድ ዓመት የሚያገለግል የጭስ (emission) እና የደህንነት ምርመራ ይደረግላቸዋል።

ምንም እንኳን የተሽከርካሪ ምርመራ በመደበኛ የሥራ ሰዓት በቅድሚያ- የመጣ ቅድሚያ -ይገልገል መርህ የሚከናወን ቢሆንም፤ የኦንላይን የምርመራ ጣቢያ የቀጠሮ መያዣ ሲስተምን (Inspection Station Appointment Scheduling System ) በመጠቀም የቅድሚያ ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።

የምርመራ ስቲከር ከፊት መስታዋቶ (ዊንድሺልድ) ላይ ከተነሳ በሃላ "VOID" (“የማይሰራ”) የሚል ያሳያል። የፊት መስታዋቶ (ዊንድሺልድዎ) ከተቀየረ ወደምርመራ ጣቢያ በ72 ሰዓት ውስጥ በመሄድ የምርመራ ስቲከርዎን ይተኩ።ምትክ ለማግኘት ክፍያ መፈጸም ግድ ነው።

ከግዴታ ነጻ የመሆን እና ቀሪ የሚሆኑ ሁኔታዎች

ለግል አገልግሎት ብቻ የሚውሉ እና የአምራች የምንጭ ማረጋገጫ (Manufacturers Certificate of Origin) ያላቸው አዲስ ተሽከርካሪዎች  የመጀመሪያውን የጭስ (emission) ምርመራ ማድረግ አይጠበቅባቸውም። ይሁንና እነዚህ አዲስ ተሽከርካሪዎች በዲኤምቪ የተሰጠ የኢንስፔክሽን ስቲከር ሊያሳዩ ይገባቸዋል። የተሽከርካሪው ምዝገባ በየጊዜው ሊታደስ ይገባል። ነገር ግን ቅድመ-1968 የሆኑ እና ጭስ አልባ (zero emission) የሆኑ የተጓዥ ተሽከርካሪዎች (passenger vehicles) ምርመራውን የማካሄድ ግዴታ የለባቸውም።

ተሽከርካሪዎ የጭስ ምርመራውን (emission test) ማለፍ ካልቻለ ፈቃድ ካለው መካኒክ የተሰጠ የ$835 የጭስ ጥገና (emission repairs) ደረሰኝ በማቅረብ ለሁለት ዓመት ከጭስ ምርመራ (emission inspection) ነጻ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምርመራን መውደቅ

ተሽከርካሪዎ የመጀመርያውን ወይም የዕድሳት ምርመራ ሳያልፍ ከቀረ ለ20 ቀን የሚቆይ “ምርመራ አላለፈም” የሚል ስቲከር በተሽከርካሪው ላይ ይለጠፋል። በተጨማሪም፣ ምርመራውን ያላለፉትን ዕቃዎች የሚያሳይ ዝርዝር ሪፖርት ይሰጦታል። ማናቸውም ጥያቄ ወይም ችግር በምርመራ ጣቢያ ለሚገኝ የመፍትሄ አስተባባሪ (resolution coordinator) ሊቀርብ ይገባል። 

ተሽከርካሪዎ ከመመዝገቡ በፊት ምርመራውን ማለፍ ይኖርበታል።

የተሽከርካሪ እንደገና-ምርመራ(ሪ-ኢንስፔክሽን)

ምርመራን የወደቀ ተሽከርካሪ ያላቸው ግለሰቦች የወደቁበትን ቦታዎች ያለበት መረጃ ያለው የመመሪያ ወረቀት ይሰጣቸዋል።

ተሽከርካሪ የመጀመሪያውን ወይም የእደሳ ምርመራን ከወደቀ፣ የወደቀበት ማሳሰቢያ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ ባሉት 20 ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን እንደገና ማስመርመር አለቦት። ምርመራን ከወደቀ በሃላ ባሉት 20 ቀናት ውስጥ ሁለት የነጻ እንደገና ማስመርመሪያ ለማግኘት ብቁ ይሆናሉ። በ20 ቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ግዜ ለማስመርመር ወይም ከ20 ቀናት በሃላ እንደገና ለማስመርመር መክፈል አለቦት፣ እናም ሙሉ ምርመራ ይደረጋል።

ተሽከርካሪ በተመደበው 20 ቀናት ውስጥ እንደገና ካልተመረመረ፣ የምርመራ የዘገየበት ክፍያ (Inspection Late Fee) ይኖረዋል። ሁሉም የምርመራ ክፍያዎች፣ ምርመራ የዘገየበት ክፍያን ጨምሮ፣ የተሽከርካሪው ምዝገባ በሚታደስበት ወቅት መከፈል አለበት። በምርመራ ጣቢያዎቹ ምንም አይነት ክፍያ አይደረግም።

የተሽከርካሪ ምርመራ (Vehicle Inspection) ማደስ

የተሳፋሪ ተሽከርካሪዎች(ፓሴንጀር ቬህክል) የኢሚሽን  ምርመራን(ኢንስፔክሽን) በየሁለት አመቱ ማለፍ አለባቸው። የተሽከራካሪዎ ምርመራ ከመቃጠሉ ከ60 ቀናት በፉት የማደሻ ማሳሰቢያው በፖስታ ወይም በኢሜል ይደርሶታል።

የተሽከርካሪ ምርመራ (Vehicle Inspection) ክፍያ

ሁሉም የተሽከርካሪ ምርመራዎች፣ ምርመራ የዘገየበት ክፍያን እና እንደገና ማስመርመሪያ ክፍያን ጨምሮ፣ የተሽከርካሪው ምዝገባ ሲደረግ እና ምዝገባ በሚታደስበት ወቅት ይከፈላል።

 

የተሽከርካሪ ምርመራ ክፍያ
አዲስ የተሽከርካሪ ምርመራ ስቲከር $10.00/4 አመት
የተሳፋሪ ተሽከርካሪ $35.00/2 አመት (በ20 ቀናት ውስጥ የሚደረጉ ሁለት የእንደገና ምርመራዎችን ያካትታል)

የንግድ ተሽከርካሪዎች
$35.00/1 አመት
(በ20 ቀናት ውስጥ የሚደረጉ ሁለት  የእንደገና ምርመራዎችን ያካትታል)
ምርመራ የዘገየበት ክፍያ $20.00 በ 30-ቀናት ግዜ ውስጥ ወይም የዚያን ከፊል
(ጣሪያው $480.00 የሆነ)
እንደገና ማስመርመሪያ ክፍያ
$35.00
(የመጀመሪያው የ20-ቀናት የምርመራ ግዜ ካለፈ በሃላ የሚሰራ)
የምርመራ ስቲከር መተኪያ $10.00

 

የተሽከርካሪ ምርመራ ጣቢያ
1001 Half Street, SW
Washington, DC 20024
ስልክ: 311 or (202) 737-4404

የፎል/ዊንተር ሰአታት:
ከሴፕቴምበር የመጀመሪያው ማክሰኞ አንስቶ የሚሰራ
የተሽከርካሪ ምርመራ: 7am - 3pm፣ ማክሰኞ – ቅዳሜ
የልጅ የመኪና ውስጥ መቀመጫ (ካርሲት) መግጠም: 7am - 3pm፣ ማክሰኞ እና እሮብ

ስፕሪንግ/ሰመር ሰአታት:
ከጁን የመጀመሪያው ማክሰኞ አንስቶ የሚሰራ
የተሽከርካሪ ምርመራ: 6am - 2pm፣ ማክሰኞ – ቅዳሜ
የልጅ የመኪና ውስጥ መቀመጫ (ካርሲት) መግጠም: 6am - 2pm፣ ማክሰኞ እና እሮብ

 

ማስታወሻዎች:
• አረጋውያን ዜጎች(ሲኔር ሲትዝንስ) የምርመራ ጣቢያው ጋር ሲመጡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ይደረግላቸዋል። የወረፋው መጀመሪያ ጋር መጥተው አረጋዊ(ሲኔር) መሆናቸውን በሩ ላይ ላለው የምርመራ ጣቢያ ተቀጣሪው ማሳወቅ አለባቸው።
• በጣም የሚጨስ ተሽከርካሪ አይመረመርም።
• ወደ ምርመራ ጣቢያው የቤት እንስሳትን አያምጡ።
• በምርመራ ጣቢያው ላይ ያለው የተሽከርካሪው ማይሌጅ ወደሚቀርበው የታችኛው ሺህ ተጠጋግቶ ይመዘገባል። ይህ የኢንደስትሪው ስታንዳርድ ነው።

የተሽከርካሪ ባለቤትነት ሰነድ(ታይትል)  << back to top >>

ለተሽከርካሪ የባለቤትነት ደብተር(ታይትል) ለማግኘት የሚከተሉት የማስረጃ ወረቀቶች ያስፈልጋሉ:

• የባለቤትነት ሰነድ (ታይትል)/የመጣበት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (Certificate of Origin) (ግልባጥ(ፎቶኮፒ) ተቀባይነት የለውም)
• የዲሲ የመንጃ ፈቃድ ወይም የዲሲ የመንጃ ያልሆነ መታወቂያ ወረቀት
• የመኪና የሽያጭ ወረቀት (ቢል ኦፍ ሴል)
• ትክክል የሆነ የኦዶሜትር ንባብ ማረጋገጫ - የተሽከርካሪው ማይሌጅ ማረጋገጫ
            • የአሻሻጭ የኦዶሜትር ንባብ ወረቀት
            • ከባለቤትነት ደብተሩ(ታይትሉ) ጀርባ  የኦዶሜትር ማይሌጅ ማረጋገጫ(በሚፈረምበት ግዜ)
            • የአሻሻጭ(ዲለር) መልሶ ማስተላፈያ ቅጹ ላይ ያለ የማይሌጅ ማረጋገጫ(ካሻሻጭ(ከዲለር) ከተገዛ )
            • የዲሲ የተሽከርካሪ ምርመራ(ኢንስፔክሽን) ሰርተፍኬት
            • የጨረታ(ኦክሽን) የሽያጭ ወረቀት(ቢል ኦፍ ሴል ) (ታይትል ብቻ ግብይት)
• የመያዟ (ሊን) ውል (የሚመለከተው ከሆነ)
• የሊዝ ውል (የሚመለከተው ከሆነ)

ተጨማሪ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ደብተር (ታይትል) መረጃ
• ለውጥ የተደረገበት ታይትል ተቀባይነት የለውም።
• ግለሰቡ ተሽከርካሪውን ያገኙት የተሽከርካሪው ባለቤት በመሞታቸው ምክንያት ከሆነ የተሽከርካሪውን ታይትል ለማግኘት ተጨማሪ የማስረጃ ወረቀቶች ማቅረብ ያስፈልጋል።
• ታይትል ከአንድ በላይ ባለቤት ሊኖረው ቢችልም፣ ዋናው ባለቤት የዲስትሪክት ነዋሪ ወይም ዲሲ ላይ የተመሰረተ ንግድ መሆን አለበት። ግለሰቡ የጋራ ባለቤት ካላቸው እና የጋራ ባለቤቱ የዲሲ ነዋሪ ካልሆኑ፣ የጋራ ባለቤቱ የሚሰራ ፎቶ ያለው መታወቂያ ማቅረብ አለባቸው። 
• ሳሊቬሽን መኪና(ዎች) ታይትል ለማግኘት የደህንነት ምርመራን(ሴፍቲ ኢንስፔክሽን) ማለፍ አለባቸው።

 

የተሽከርካሪ ባለቤትነት ደብተር (ታይትል) ክፍያ

ታይትል ክፍያ
የተሽከርካሪ ታይትል ብቻ (አዲስ እና መተኪያ)   $26.00
እንደገና ታይትሉን ማውጣት  $26.00
መያዣ ተደርጎ የነበረን ማስመዝገቢያ(ሊን ሪኮርዴሽን) (ተሽከርካሪው በብድር ከሆነ)        $20.00/መያዣ(ሊን)
3,499 lbs ወይም ከዚያ በታች ለሆኑ ተሽከርካሪ ኤክሳይስ ታክስ  ፌር የገበያ ዋጋውን 6%
ከ 3,500 lbs - 4,999 lbs ለሆነ ተሽከርካሪ ኤክሳይስ ታክስ ፌር  የገበያ ዋጋውን 7%
5,000 lbs ወይም ከዚያ በላይ ለሆነ ተሽከርካሪ ኤክሳይስ ታክስ ፌር የገበያ ዋጋውን  8%
ለሀይብሪድ ተሽከርካሪዎች ኤክሳይስ ታክስ 0%

     
        

የተሽከርካሪ ታርጋዎች << back to top >>

የዲሲ ነዋሪዎች፣ አንዱ ከተሽከርካሪው ከፊት አንዱ ከሃላ የሆኑ ሁለት የዲሲ ታርጋ ዎችን ማሳየት አለባቸው፣ ከሚከተሉት በስተቀር:

• ሞተርሳይክል
• ሞፔዶች
• ትሬለሮች

ለነዚህ ከተሽከርካሪው ከሃላቸው አንድ ታርጋ ብቻ ማሳየት ነው ያለባቸው። ታርጋዎች በደንብ የሚታዮ እና  በምንም ነገር ያልተከለሉ/ያልተሸፈኑ መሆን አለባቸው፡፡

ታርጋ መተካት

ከጠፋቦት፣ ከተሰረቀቦት ወይም በማርጀቱ ምክንያት እንዲተካሎት ከፈለጉ፣ ዲኤምቪ የተሽከርካሪዎን ታርጋዎን/ታርጋዎቾን ይተካሎታል። የታርጋዎችን ምትክ ለማግኘት፣ የዲኤምቪ የአገልግሎት ማእከል ይጎብኙ እና የሚከተሉትን የማስረጃ ወረቀቶች ዋናው(ሮቶኮፒ ያልሆነ) ያቅርቡ እና ተገቢውን ክፍያ ይክፈሉ።

• የተሽከርካሪ ምዝገባ ካርድVehicle Registration Card
• የተመዘገበው ባለቤት(ባለቤቶች) የሚሰራ መታወቂያ
• አሁን ያለው ታርጋዎች (አርጅቶ ከሆነ፣ ወይም አንዱ ብቻ ጠፍቶ ወይም ተሰርቆ ከሆነ)
ማስታወሻ: አሁን ያለውን ታርጋዎን ካላስረከቡ በዚያ ታርጋ ለሚመጣውን ማንኛውንም ትኬቶች ሃላፊነት ሊኖርቦት ይችላል። በተጨማሪም፣ ለጠፋ ወይም ለተሰረቀ ታርጋዎች የፖሊስ ሪፖርት ያስፈልጋል።

ታርጋ ማዘዋወር

ለአሮጌ ወይም ለአዲስ ተሽከርካሪ የታርጋ ማዘዋወርን መጠየቅ ይችላሉ። የታርጋ ማዘዋወር አሁን ያሎትን ታርጋዎች ወደሌላ ተሽከርካሪ ማዘዋወርን ያስችሎታል። ባለቤቱ ሌላ ከሆነ ወይም ታርጋዎቹ ቀናቸው ተቃጥሎ ከሆነ ታርጋዎችን ወደሌላ ተሽከርካሪ ማስተላለፍ አይቻልም።

በሚከተሉት የማስረጃ ወረቀቶች ታርጋዎትን ማዘዋወር ይችላሉ:

• ታርጋው ያለበት ተሽከርካሪ ወቅታዊ የተሽከርካሪ ምዝገባ
• ወቅታዊ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ደብተር(ታይትል)
• የሚሰራ የተሽከርካሪዎች ምርመራ(ኢንስፔክሽን)
• የሚሰራ የዲሲ ኢንሹራንስ ፖሊሲ
• የሚሰራ የዲሲ የመንጃ ፈቃድ/መታወቂያ ወረቀት

ታርጋ ማስረከብ

የሚከተሉት ከሆነ፣ ታርጋዎትን ለዲኤምቪ መመለስ አለቦት:

• ከዲስትሪክቱ ውጭ መኖር ከጀመሩ
• ኢንሹራንሶ ከተሰረዘ
• መኪናዎትን ከሸጡ ወይም ለእርዳታ(ዶኔሽን) ከሰጡ እና የተሽከርካሪዎን ታርጋዎች ወደሌላ ተሽከርካሪ ካላዘዋወሩ።
• ከታርጋዎ አንዱ ተሰርቆ ነበር እና የታርጋዎችን ምትክ አግኝተዋል።
• ምዝገባዎን ሰርዘውታል
• ታርጋዎን ወደ ጉዳተኞች፣ ፐርሰናላይዝድ ወይም የድርጅት ታርጋዎች ከቀየሩ
• ያረጁ ታርጋዎችን ምትክ ከወሰዱ

ታርጋዎን ለማስረከብ:

በኢንተርኔት(የኦንላይን) ታርጋ መሰረዣን ይጠቀሙ ወይም
• ወደ ሚከተለው በፖስታ ይመልሱ :

DC DMV
Vehicle Registration
P.O. Box 90120
Washington, DC 20090

• ከዲኤምቪ ደረሰኝ በፖስታ እንልክሎታለን። የኢንሹራንስ ክፍተት ክፍያ እንዳይጣልቦት፣ ኢንሹራንሶን ከመሰረዞ በፊት ታርጋ አስረክበዋል የሚል ደረሰኝ እስከሚቀበሉ ድረስ መጠበቅ አለቦት።

የማቆምያ(ፓርኪንግ) ፈቃዶች/የቅይይር ስቲከሮች(Reciprocity Stickers)  << back to top >>

በዲስትሪክት የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (District Department of Transportation (DDOT) ምትክ ሆኖ መስረፍቶቹን ለሚያሟሉ ሰዎች ዲኤምቪ (DMV) ለልዩ የማቆምያ መብቶች ፈቃዶችን ያትማል፣ እንዲሁም፣  የተሽከርካሪ ምዝገባ የቅይይር (reciprocity) መብቶችን  ለሚከተሉት ይሰጣል :

• የሌላ ግዛቶች ( jurisdictions) ቋሚ ነዋሪ ሆነው ህጉ በዲሲ የቅይይር(reciprocal) ነዋሪነትን መብትን የፈቀደላቸው።
• የዲስትሪክት ታርጋን ለማውጣት አቅማቸው የሚገድባቸው አንዳንድ የዲሲ ነዋሪዎች።

እባኮን፣ የቅይይር መብቱ (reciprocity) የማቆሚያ መብት እንዳልሆነ ያስታውሱ።

የነዋሪ የማቆሚያ (ፓርኪንግ) ፈቃድ አርፒፒ (RPP)

አርፒፒ (RPP) በዲሲ የተመዘገበ ተሽከርካሪ፣ ወይም የቅይይር መብት (reciprocity) ያለውን ተሽከርካሪ የመኖሪያ ማቆሚያ አድራሻ ተብሎ በተመደበ አካባቢ ያለገደብ ለማቆም ያስችላል። ለአርፒፒ (RPP) ብቁ ለመሆን፣ ጎዳናዎ በዲዲኦቲ (DDOT) ለአርፒፒ (RPP) ዞን ተብሎ የተመደበ መሆን አለበት፡፡

የነዋሪ የማቆምያ ፈቃዶች በዲኤምቪ (DMV) የሚታተሙት (የሚሰጡት) የተሽከርካሪ ማስመዝገብ አገልግሎት አካል ሆኖ ነው። አመልካቾች፣ የዲኤምቪ (DMV) የአገልግሎት ማእከል ሄደው የሚከተሉትን የማስረጃ ወረቀቶች ማቅረብ እና ተገቢውን የማቆምያ ፈቃድ ክፍያ መክፈል ይችላሉ።

• የሚሰራ የዲሲ የተሽከርካሪ ምዝገባ ካርድ
• የሚሰራ የዲሲ የመንጃ ፈቃድ ወይም የሚሰራ የዲሲ የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ ወረቀት

ወይም

• የሚሰራ የዲሲ የቅይይር ፈቃድ (Reciprocity Permit)

የሚሰራ (ትክክል የሆነ) የተሽከርካሪ ምዝገባ ካሎት እና ለአርፒፒ( RPP) ብቁ ከሆኑ፣ አርፒፒ(RPP)ን  በኦንላይን(በኢንተርኔት) መጠየቅ ይችላሉ።

ዲሲ ዲኤምቪ (DC DMV) የተለያዩ ግዚያዊ የማቆምያ ፈቃዶችን ይሰጣል፣ እንደ የጤና አገልግሎት ሰጭዎች፣ ለእንግዶች የጎብኝዎች የማቆምያ ፈቃድ (ይህንን በአቅራቢያዎ ካለ የፖሊስ ጣቢያ ማግኘት ይችላሉ)፣ የኮንትራክት ተቀጣሪዎች፣ የዲሲ ነዋሪዎች አዲስ መኪና እና የዲሲ ነዋሪዎች የኪራይ መኪና ላሉ።

በተጨማሪም፣ ዲሲ ዲኤምቪ በርካታ የቅይይር (reciprocity) ፈቃዶችን ይሰጣል፣ እንደ ግዚያዊ ነዋሪዎች፣ የከፊል ግዜ (ፓርት ታይም) ነዋሪዎች፣ ሙሉ ግዜ ተማሪዎች፣ ለኮንግረንስ አባላት ወይም ለግል ሰራተኞቻቸው፣ የፕሬዝዳንቱ ሹሞች፣ በስራ ላይ ያሉ የጦር ሀይል፣ ዲፕሎማቶች እና የዲሲ ነዋሪዎች ሆነው እቤት የሚወሰድ የድርጅት መኪና ካላቸው።

ስለግዜያዊ የማቆምያ ፈቃድ ወይም የቅይይር (reciprocity) ፈቃድን ስለማግኘት ለበለጠ መረጃ፣ የስልክ ማእከሉን በ  311 or 202-737-4404 ያግኙ።

የጉዳተኞች ታርጋ እና የጉዳተኞች የማሳያ ካርድ   << back to top >>

ዲኤምቪ (DMV) በዲስትሪክት የትራንስፖርቴሽን ዲፓርትመንት (District Department of Transportation (DDOT) ስም ሆኖ የጉዳተኞችን የማሳያ ካርድ እና ፈቃዶችን ይሰጣል፡፡

የግዜያዊ እና የረጅም-ግዜ የማሳያ ማመልከቻ በሀኪሞ የሚሞላ ክፍልን ያካትታል። ለአንድ ሳምንት ፈቃድ ምንም አይነት የሀኪም ማረጋገጫ አያስፈልግም። ማመልከቻዎች በፖስታ ለ DC DMV, ATTN: Disability Services, PO Box 90120, Washington, DC 20090 መላክ፣ በፋክስ ወደ (202) 673-9908 መላክ ወይም ወደ ማንኛውም የዲኤምቪ የአገልግለቶት ማእከል ሊወሰዱ ይችላሉ።  

ጥያቄዎ ተቀባይነት ካገኘ፣ የአንድ ሳምንት ፈቃድ ሊሰጦት ይችል ይሆናል ወይም የግዜያዊ የማሳያ ካርድ(እስከ ስምንት አመት ድረስ) ወይም የረጅም-ግዜ የማሳያ ፈቃድ(የመንጃ ፈቃዶ ወይም መታወቂያዎ የሚቃጠልበት ግዜ ጋር አንድ ላይ እንዲሆን ስምንት አመት) ሊሰጦት ይችል ይሆናል።የዲሲ ነዋሪ ለሆነ አንድ አመልካች አንድ የማሳያ ካርድ አና አንድ ጥንድ የተሽከርካሪ ታርጋ ሊሰጥ ይችል ይሆናል።

ለጉዳተኞች ማሳያ ምንም ክፍያ የለውም። ለጉዳተኛ ማሳያ ካርድ ማመልከቻዎን ከሁለቱ በአንዱ መንገድ ማስፈጸም ይችላሉ:

• በፖስታ
• በአካል በዲኤምቪ የአገልግሎት ማእከል

የጉዳተኞች የማቆምያ ማሳያ ካርድ ከፊት ለፉት መስኮት መታየት እና መነበብ የሚችል መሆን አለበት፣ እናም ለማቆም(ፓርኪንግ) እና ህግ አስፈጻሚ ሹማምንት ለማሳየት የዲኤምቪ የማሳያ ካርድ ደረሰኝ መኖር አለበት።

ለግለሰቦች የግዚያዊ የዲሲ የመመዝገቢያ እና የግዚያዊ ታርጋዎች 

የግዜያዊ የዲሲ መመዝገቢያ የሚሰጠው ከስቴት ውጭ የሆነውን ምዝገባቸውን ወደ ዲሲ ከማዘዋወራቸው በፊት ተሽከርካሪያቸውን ለምርመራ መውሰድ ላለባቸው የዲሲ ነዋሪዎች ወይም ከምዝገባ በፊት በኢንስፔክሽን ማለፍ ያለበት አሮጌ(ከዚህ በፉት ጥቅም ላይ የዋለ) ተሽከርካሪ ለገዙ የዲሲ ነዋሪዎች ነው። ግዜያዊ የዲሲ ምዝገባ ለ 45-ቀናት የሚሰጥ መደበኛ የተሳፋሪ ጠንካራ ታርጋ ነው።

ተሽከርካሪው አንዴ ከተመረመረ በሃላ፣ ምዝገባዎን በኦንላይን(በኢንተርኔት) ወይም በፖስታ ማሳደስ ይችላሉ።

ቀድሞ የነበረ፣ ቀኑ ያልተቃጠለ የዲሲ ምርመራ(ኢንስፔክሽን) ያለው አሮጌ(ከዚህ በፉት ያገለገለ) ተሽከረካሪ ከገዙ፣ ግዜያዊ የዲሲ ታርጋ አይሰጦትም። ተሽከርካሪውን ታይትል/ምዝገባ ሲያደርጉለት ያልተቃጠለው የዲሲ ምርመራ(ኢንስፔክሽን) ይቀጥልሎታል።

የሚከተለው ለዲሲ የግዚያዊ ምዝገባ አኪያሄድ ነው:

 

• የግዜያዊ የዲሲ ምዝገባ ለማግኘት የሚያስፈልጉ የማስረጃ ወረቀቶች
        • የባለቤትነት(ታይትል) ሰርተፍኬት (Certificate of Title)/ የግዜያዊ ታርጋ ማመልከቻ
        • በአግባቡ ለማስተላለፍ የተፈረመ(ኢንዶርስ የተደረገ)  ታይትል
        • የሚሰራ የዲሲ ኢንሹራንስ ማረጋገጫ
        • የዲሲ ፈቃድ ወይም የዲሲ የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ
        • አግባብ ያለው የግዚያዊ ዲሲ ምዝገባ፣ ታይትል እና የመያዣ ባለቤት (ሊን ሆልደር) ክፍያ

• የግዚያዊ የዲሲ ምዝገባዎን ሊያገኙ ሲሉ፣ ከታይትል ሂደት ጋር የተያያዙ ሁሉኑም ክፍያዎች ይከፍላሉ (ማለትም፣ ኤክሳይስ ታክስ፣ የታይትል ክፍያ እና ሊን ሪኮርዴሽን ክፍያዎች(የሚመለከቶ ከሆነ))
• የግዜያዊ የዲሲ የምዝገባ ክፍያ እና ማንኛውንም የአርፒፒ (RPP) ክፍያዎች
• “የግዚያዊ ምዝገባ” ("Temporary Registration") የሚሉት ቃላት የመስታዋቱ የምዝገባ ስቲከር ላይ ይጻፋል
• የህግ አስፈጻሚዎች እና ፓርኪን መኮንኖች የሚሰራ የኢንስፔክሽን ስቲከር ሳይኖር የግዚያዊ የዲሲ ምዝገባን እንደሚሰራ ያውቃሉ።

ሁለተኛ የግዚያዊ የዲሲ ምዝገባ ሊሰጦት ስለማይችል፣ ወዲያውኑ ተሽከርካሪዎን ወደ ምርመራ(ኢንስፔክሽን) በመውሰድ አስፈላጊውን ጥገና ከ 45-የሚቃጠልበት ቀናት በፊት እንዲጠናቀቅ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

 

የግዜያዊ የወረቀት ታርጋ

ወረቀት የሆኑ የ45-ቀናት የግዚያዊ የወረቀት ታርጋዎች የሚሰጡት ለ:

• በቅርቡ ዲሲ ውስጥ አሮጌ(ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የዋለ) ተሽከርካሪ ለገዙ የስቴት ውጭ ለሆኑ ነዋሪዎቸ
• መያዣ ያዚው(ሊን ሆልደሩ) ከስቴት ውጪ የሆነውን ታይትላቸውን እንዲሰጣቸው የሚጠባበቁ፣ እና ቀኑ የተቃጠለ የዲሲ ውጪ ታግ ያላቸው የዲሲ ነዋሪዎች
• ከምዝገባ በፊት በምርመራ (ኢንስፔክሽን) ጣቢያው መመርመር እና መደባቸው መለየት ያለባቸው የሳልቬሽን ተሽከርካሪዎች

ለግዚያዊ የወረቀት ታርጋዎች የሚከተሉት ሂደቶች ይደረጋሉ:

• የግዚያዊ የወረቀት ታርጋን ለማግኘት የሚያስፈልጉ የወረቀት ማስረጃዎች
         • ባለቤትነት(ታይትል)ሰርተፍኬት (Certificate of Title)/ የግዜያዊ ታርጋ ማመልከቻ
         • በአግባቡ ለመተላለፍ የተፈረመ(ኢንዶርስ የተደረገ) ታይትል
         • የሚሰራ የዲሲ ኢንሹራንስ ማረጋገጫ
         • የዲሲ ፈቃድ ወይም የዲሲ የመንጃ ያልሆነ የመታወቂያ
         • አግባብ ያለው የግዚያዊ የወረቀት ታርጋ ክፍያ

• የግዚያዊ የወረቀተት ታርጋ ክፍያ እና ማንኛውም አግባብ ያለው የአርፒፒ  (RPP) ክፍያ
• የህግ አስፈጻሚዎች እና ፓርኪን መኮንኖች ተሽከርካሪው የሚሰራ የኢንስፔክሽን ስቲከር ሳይኖረው የግዚያዊ የወረቀት ታርጋው እንደሚሰራ ያውቃሉ።

የተሽከርካሪ አገልግሎት ቅጾች እና ኦንላይን(የኢንተርኔት) ማስፈጸሚያዎች(ትራንዛክሽንስ)  << back to top >>

ለተጎጅዎች የማሳያ ካርድ እና ታርጋዎች ማመልከቻ
የባለቤትነት ደብተር(ሰርተፍኬት ኦፍ ታይትል)/ የግዚያዊ ታርጋ ማመልከቻ 
የመያዣ ባለቤት (ሊን ሆልደር) ከስቴት ውጪ የሆነ ታይትል መጠየቂያ
ለምርመራ(ለኢንስፔክሽን) በኦንላይን ቀጠሮ ማስያዣ
ከስቴት ውጪ ታይትል ያለበት ሁኔታ በኦንላይን 
በኦንላይን ምዝገባ መተኪያ(ሪፕሌስመንት) 
ኦንላይን የነዋሪ የማቆሚያ ፈቃድ
ኦንላይን ታርጋ መሰረዣ
ኦንላይን የተሽከርካሪ ምዝገባን እና የነዋሪ ማቆሚያን ማሳደሻ
የተሽከርካሪ የህግ ውክልና ማመልከቻ


የታረመበት:  ማርች 24፣ 2014