Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dmv

Department of Motor Vehicles
 

DC Agency Top Menu

-DC DMV will no longer prevent DC residents from applying for a new or renewed driver’s license because of failing to meet the requirements of the Clean Hands Law.

-A +A
Bookmark and Share

Adjudication Services Amharic

የዳኝነት አገልግሎት  

የዳኝነት አገልግሎት በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ውስጥ ለተሰጡ ትኬቶች የአስተዳደራዊ ዳኝነቶችን እና በአካል ትኬት መክፈል አገልግሎቶችን ይሰጣል።

መሰረታዊ የዳኝነት አገልግሎቶች መረጃ
ትኬት መክፈል
የማቆምያ(ፓርኪንግ) እና የፎቶ ማስፈጸሚያ ትኬት ዳኝነት መረጃ
በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የተደረገ አነስተኛ ጥሰት ትኬት ዳኝነት መረጃ
ትኬቶን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ እንደገና እንዲታይ መጠየቅ 
ትኬቶን በተመለከተ የተሰጠ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ማለት
ሌሎች የዳኝነት አገልግሎቶች መረጃ
የዳኝነት ቅጾች እና የኦንላይን(የኢንተርኔት) ግብይት(ማስፈጸሚያ)

መሰረታዊ የዳኝነት አገልግሎቶች መረጃ <<back to top>>

የዲሲ ዲኤምቪ (DC DMV) ትኬቶችን አይሰጥም። የማቆምያ (ፓርኪንግ)፣ የፎቶ ማስፈጸሚያ፣ እና በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የተደረገ የአነስተኛ ጥሰት ትኬቶችን የሚሰጡት የህዝብ ስራዎች ዲፓርትመንት (Department of Public Works (DPW)፣ የዲሲ የትራንስፖርቴሽን ዲፓርትመንት (DC Department of Transportation (DDOT) እና እንደ የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንትን (Metropolitan Police Department) ጨምሮ በህግ አስፈጻሚ ኤጀንሲዎች መኮንኖች (ኦፊሰሮች) ናቸው።

የመንጃ ፈቃድ መታገድ፣ መሻር፣ እና መልሶ መስጠት ዳኝነቶችም በዳኝነት አገልግሎቶች ይደረጋሉ። 

የማቆምያ (ፓርኪንግ) እና የፎቶ ማስፈጸሚያ ክርክሮች በፖስታ እና ያለ ቀጠሮ በአካል በመገኘት በዳኝነት አገልግሎቶች ይሰጣል። የተጠቀሰው ተሽከርካሪ የተመዘገቡ ባለቤት ወይም ደግሞ በተመዘገበው ባለቤት የተሞላ የውክልና ስልጣን ቅጽ ሊኖሮት ይገባል። በተጨማሪ፣ የዳኝነት ጥያቄ በኦንላይን(በኢንተርኔት) ማስገባት ይችላሉ።

በአካል በመገኘት የሚደረገው  በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ የተደረገ የአነስተኛ ጥሰት ዳኝነቶች ቀጠሮ መያዝ አለበት፤ ትኬቱን የሰጠው መኮንን (ኦፊሰር) መጥሪያ ይሰጠዋል፣ በአካል በሚደረገው ዳኝነት ይቀርባል። ያለ ቀጠሮ በአካል በመምጣት ሊደረጉ አይችሉም፣ ነገር ግን፣ በፖስታም ሊደረጉ ይችላሉ።

ለመንጃ ፈቃድ ዳኝነቶች ቀጠሮ መያዝ አለበት።

ትኬት መክፈል  <<back to top>>

የክፍያ የግዜ ገደቦች እና ዘዴዎች

ዲኤምቪ (DMV) በትኬቱ ከተመለከተው ቀን ጀምሮ ባሉ 30 የመቁጠሪያ (ካላንደር) ቀናት ውስጥ ክፍያዎን መቀበል አለበት። ነገር ግን፣  በ30 የአቆጣጠር (ካላንደር) ቀናት ውስጥ ካልከፈሉ፣ የገንዘብ ቅጣቱን ልክ የሚያክል መቀጮ ይጨመራል። ዲኤምቪ (DMV) አራት የክፍያ አማራጮችን ይሰጣል፡ በኦንላይን (በኢንተርኔት)፣ በፖስታ፣ በአካል ወይም በስልክ በ (866) 893-5023። የዋና የፋይናንስ ሹም ቢሮ ማዕከላዊ የመሰብሰብያ ክፍል (Chief Financial Officer Central Collection Unit) በ(202) 727-0771 ደውለው በማነጋገር፣ ለዳኝነት ለመቅረብ ብቃታቸው ያበቃባቸውን ትኬቶቾን በትንሽ በትንሹ (ኢንስቶልመንት) የመክፈል መስፈርቱን ሊያሟሉ ይችሉ ይሆናል። በአጠቃላይ፣ ለአከፋፈል ዕቅድ (ፔይመንት ፕላን) ብቁ ለመሆን፣ የትኬትዎ  ዕዳ $350 ወይም ከዛ በላይ መሆን ይኖርበታል።

በኦንላይን (በኢንተርኔት)

በኦንላይን (በኢንተርኔት) የሚያስገቡት መረጃ በፅኑ የሶስተኛ-አካል ድህረ-ገጽ የተጠበቀ ነው፣ እና በምንም ምክንያት አይሰራጭም። የዲሲ መንግስት የቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ እና ዲስካቨርን ይቀበላል። የዲሲ መንግስት አሜሪካን ኤክስፕረስ አይቀበልም።

       • የማቆምያ(ፓርኪንግ) እና/ወይም የፎቶ ማስፈሚያ ጥሰቶችን መክፈል (የትኬት ቁጥሮቹ በፊደል ጀምረው እስከ ዘጠኝ በሚሆኑ አሀዞች ሊከተሉ ይችላሉ፣ ወይም ሁሉም አሀዞች ሊሆኑ ይችላሉ።)
       • በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ለተደረጉ አነስተኛ ጥሰቶች መክፈል (የትኬት ቁጥሮቹ ሁሉም አሀዞች ናቸው።)

በፖስታ

       • የቼክዎ ወይም የመኒ ኦርደርዎ ተከፋይ DC Treasurer ያድርጉት (ጥሬ ገንዘብ አይላኩ)፣ እናም ክፍያዎ ላይ የትኬቱን ቁጥር ይጻፋ። ትኬቱን አብረው ይላኩ፣ ወይም ትኬትዎ ከሌልዎት የተሽከርካሪውን ክልል (ስቴት) እና ታርጋ ቁጥር በቼክዎ ወይም መኒ ኦርደርዎ ላይ ይጻፉ (ለምሳሌ፣ የዲሲ የሠሌዳ ታርጋ ቁጥር #123456)።
       • የማቆምያ (ፓርኪንግ)፣ የፎቶ ማስፈጸሚያ ወይም በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የተደረገ ጥሰት እና ቼክ ወይም መኒ ኦርደር ለሚከተለው ይላኩ፡

       DMV Adjudication Services
       PO Box 2014
       Washington, DC 20013

በአካል

       • የዳኝነት አገልግሎቶች ክፍያዎችን ይቀበላል።
       • ትኬትዎን ይዘው ከመጡ፣ ትኬትዎን ለመክፈል የገንዘብ ተቀባይ ወዳለበት መስኮት ይመራሉ።
       • ትኬትዎን ሳይዙ ከመጡ፣ የትኬትዎ በኮምፒተር የታተመ (ፕሪንትኣውት) ለማግኘት መታወቅያዎን ይስጡ፣ ከዛ ትኬትዎን ለመክፈል የገንዘብ ተቀባይ ወዳለበት መስኮት ይሂዱ። 
       • በጥሬ ገንዘብ፣ በቼክ፣ በመኒ ኦርደር ወይም በክረዲት ካርድ መክፈል ይችላሉ። የዲሲ መንግስት ቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ እና ዲስካቨር ይቀበላል። የዲሲ መንግስት አሜሪካን ኤክስፕረስ አይቀበልም።
       • ለተቆለፉ (ቡት ለሆኑ) ወይም ተጎትተው ለተወሰዱ (ቶው ለተደረጉ) ተሽከርካሪዎች ለማስለቀቅ በቼክ መክፈል አይቻልም።
       • የተቆለፈ (ቡት የሆነ) በአጠቃላይ ክፍያ ከተደረገ በኋላ ባሉት ሁለት ሰዓታት ውስጥ ይለቀቃል።


የማቆምያ (ፓርኪንግ) እና የፎቶ ማስፈጸሚያ ትኬት መረጃ  <<back to top>>

የማቆምያ (ፓርኪንግ) ትኬቶች ከተሰጡበት ቀን ጀምሮ ባሉ 30 ቀናት ውስጥ ምላሽ ሊሰጥባቸው ይገባል። የፎቶግራፍ ማስፈጸሚያ ትኬቶች፣ ትኬቱ ከተላከበት ቀን ጀምሮ ባሉ 30 ቀናት ውስጥ ምላሽ ሊሰጥባቸው ይገባል። ለትኬት ምላሽ ለመስጠት ዳኝነት እንዲደረግ መጠየቅ፣ ወይም ደግሞ የገንዘብ ቅጣቱን መክፈል ይኖርቦታል። ከ30 ቀናት በኋላ፣ የዋናውን ቅጣት ክፍያውን ልክ የሚያህል የመዘግየት መቀጫ (ሌት ፔናልቲ) ይጨመራል። ከ60 ቀናት በኋላ፣ ጥፋቱን እንደ ፈጸሙ ተደርጎ ይወሰዳል፣ በሌሉበት እንደተወሰነ ተደርጎ ይወሰዳል፣ ከዚያም በሃላ በዳኝነት እንዲታይ መጠየቅ አይችሉም። በ61 እና 120 ቀናት መካከል በሌሉበት የተወሰነን ውሳኔ ለማስነሳት አቤቱታ ማስገባት (ፋይል ማድረግ) ይችላሉ። በአቤቱታዎ ላይ፣ ለትኬትዎ በትክክለኛው ወቅት ምላሽ እንዳይሰጡ ያደረጎትን ይቅር ሊባል የሚችል ቸልተኝነት የሚተነትን ማብራርያ እና ለጥሰቱ መከላከያ ማቅረብ ይኖርቦታል። የትኬት የገንዘብ ቅጣትን መክፈል ጥፋተኝነትን እንደ መቀበል ነው የሚቆጠረው። የገንዘብ ቅጣቱ አንዴ ከተከፈለበት በሃላ ትኬቱ ላይ ዳኝነት ማግኘት አይችሉም። ትኬት ከሰጠው ኤጀንሲ በ21 ቀናት ውስጥ ወደ ዲኤምቪ (DMV) ያልደረሱ ትኬቶች ወድያውኑ ይሰረዛሉ።

ያልተከፈሉ የማቆምያ (ፓርኪንግ) እና የፎቶ ማስፈጸሚያ ትኬቶች፣ ተሽከርካሪዎ እንዲቆለፍ (ቡት እንዲደረግ) ሊያደርጉ ይችላሉ። ቢያንስ ሁለት ያልተከፈሉ የማቆምያ (ፓርኪንግ) እና/ወይም የፎቶግራፍ ማስፈጸሚያ ትኬቶች ካሎት ሊቆለፍቦት (ቡት ሊደረግ) ይችላል። ያልተከፈሉ ትኬቶች ካሎዎት፣ ተሽከርካሪዎ ህግ በጠበቀ መልክ የቆመ(ፓርክ የተደረገ) ቢሆንም ሊቆለፍ (ቡት ሊደረግ) ይችላል። (ማስታወሻ፡ ዲኤምቪ ተሽከርካሪዎችን አይቆልፍም(ቡት አያደርግም)፣ ጎትቶ አይወስድም(ቶው አያደርግም) ወይም ኢምፓውንድ(አስሮ አይዝም) አያደርግም፣ እነዚህ የህዝብ ስራዎች ዲፓርትመንት (Department of Public Works) ተግባሮች ናቸው። የያልተከፈሉ ትኬቶች ለሰብሳቢዎች (ኮሌክሽን) የተጋለጡ ይሆናሉ።

በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የተደረገ ጥሰት መረጃ <<back to top>>

በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የተደረገ አነስተኛ ጥሰት ወይም የትራፊክ ትኬት፣ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉ 30 ቀናት ውስጥ ዳኝነት በመጠየቅ ወይም የትኬቱ የገንዘብ ቅጣት በመክፈል ምላሽ መሰጠት አለበት። ከ30 ቀናት በኋላ፣ የገንዘብ ቅጣቱን ልክ የሚሆን የመዘግየት መቀጫ (ሌት ፔናልቲ) ይጨመራል። ትኬቱ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉ 60 ቀናት ውስጥ ለትኬቱ ምላሽ ካልተሰጠ፣ ትኬቱ በሌሉበት እንደተወሰነ ሆኖ ይወሰዳል እናም ነጂው ለጥሰቱ ሀላፊነተ እንዳለባቸው ይወሰዳል። አንዴ ትኬቱ በሌሉበት የተወሰነ ተብሎ  ከተወሰደ በሃላ በትኬቱ ላይ ዳኝነት ሊደረግሎት አይችሉም። በሌሉበት የተወሰነን ውሳኔ ለማስነሳት አቤቱታ ማቅረብ እና ለትኬቱ ምላሽ ያልሰጡበት ወይም ቀጠሮ ላስያዙት የዳኝነት ወቅት ላለመገኘቶ ይቅር ሊባል የሚችል የቸልተኝነት ምክንያት ማሳየት እና ለትኬቱ መከላከያ ማቅረብ ይችሉ ይሆናል። ትኬት ከሰጠው ኤጀንሲ በ21 ቀናት ውስጥ ወደ ዲኤምቪ (DMV) ያልደረሱ ትኬቶች ወድያውኑ ይሰረዛሉ።

ያልተከፈሉ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የተደረጉ ጥሰቶች የመንጃ ፈቃድዎ እንዲታገድ ያደርጋሉ። በዳኝነት ሂደቱ ጥፋተኛ ኖት ተብሎ ከተወሰነ፣ እንደገና እንዲታይሎት መጠየቅ እና ተጨማሪ ማስረጃ/ሰነድ ማቅረብ ይችላሉ። ዳኝነት ከተደረገበት ቀኑ አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ  እንደገና እንዲታይሎት ካልጠየቁ ወይም ትኬቱን ካልከፈሉ የመንጃ ፈቃዶ ይታገዳል። ለትኬቱ በ60 ቀናት ውስጥ ምላሽ ካልሰጡ፣ መንጃ ፈቃድዎ ይታገዳል።
አብዛኛዎቹ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የሚደረጉ ጥሰቶች በመንጃ ፈቃድዎ ነጥቦች (ፖይንት) እንዲያዙ ያደርጋሉ። በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ 10 ነጥቦች ከተጠራቀመቦት የመንጃ ፈቃድዎ ይታገዳል፣  12 ወይም ከዛ በላይ ነጥቦች በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ ከተጠራቀመቦት ደግሞ ይሻራል።
ነጂውን የሚያግድ እና የሚያዘናጉ ነገሮች ህጎች (Driver impairment and distraction laws) በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ ውስጥ በጥብቅ ተፈጻሚነት ላይ ይውላሉ። በአጠቃላይ፣ ማንኛውም ሊለካ የሚችል የአልኮል ወይም የአንደንዛዥ ዕጾች መጠን ኖሮት በህጋዊ መንገድ የሞተር ተሽከርካሪ ማንቀሳቀስ አይችሉም። የእጅ ስልኮች (ሴልፎኖች) እጅን ነጻ የሚያደርግ መሳርያ (ሀንድስ ፍሪ ዲቫይስ) በመጠቀም ብቻ ነው እየነዱ መጠቀም የሚቻለው። እየነዱ መልእክት መላላክ (ቴክስቲንግ) በምንም ሁኔታዎች አይፈቀድም።  ሁሉም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ(ሲትቤልት) ማሰር ግዴታ ነው። የልጆች የመያዣ መቀመጫዎችም (ቻይልድ ሪስትረይንት ሲትስ) ግዴታ ናቸው፣ በጥብቅም ይፈጸማሉ።

ትኬቶችን ለዳኝነት ማቅረብያ ዘዴዎች  <<back to top>>

ለሁሉም የዳኝነት ዘዴዎች፣ ለትኬቱ ሀላፊነት እንደሌለቦት የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርቦታል። ማስረጃዎቹ፣ የፖሊስ ሪፖርቶች፣ የተመለሱ የታርጋ ደረሰኞች፣ የምዝገባ ካርዶች፣ ወዘተ ያጠቃልላሉ። ለትኬትዎ ዳኝነት ሊጠይቁ ከሆነ ለመጀመርያው ትኬት ወይም ለመቀጮው ምንም ክፍያ አይክፈሉ። የዳኝነት ጥያቄዎ በኦንላይን (በኢንተርኔት) ወይም በፖስታ የሚያስረክቡ ከሆነ፣ ማረጋገጫ ወረቀት በኢሜይል ወይም በፖስታ ይደርሶታል። የማረጋገጫ ወረቀት ካልደረሶት፣ የዳኝነት ጥያቄዎ አልደረሰንም ማለት ነው። የዳኝነት መርማሪ ውሳኔዎች በዲኤምቪ (DMV) በተመዘገበው አድራሻዎ በፖስታ ይላክሎታል። 

• የዳኝነት ጥያቄ በኦንላይን (በኢንተርኔት) ያስገቡ
• የዳኝነት ጥያቄ በፖስታ ያስገቡ:

        DMV Adjudication Services
        Attn: Mail Adjudication
        PO Box 37135
        Washington, DC 20013

• የማቆምያ (ፓርኪንግ) እና የፎቶግራፍ ትኬቶች ያለ ቀጠሮ በመሄድ ዳኝነት ለማድረግ፣ ወደ ዳኝነት አገልግሎቶች በመሄድ ይጠይቁ።
• በመንቀሳቀስ ላይ እያለ ለተደረገ ጥሰት  የሰጠው መኮንን (ኦፊሰር) ባለበት ዳኝነት ለማግኘት፣ በፖስታ፣ በኦንላይን (በኢንተርኔት) ወይም በአካል በመሄድ ቀጠሮ ያስይዙ።

ትኬቶን በተመለከተ የተሰጠውን ውሳኔ እንደገና እንዲታይ መጠየቅ <<back to top>>

በዳኝነት ወቅት ለማቆሚያ(ፓርኪንግ)፣ የፎቶ ማስፈጸሚያ ወይም በመንቀሳቀስ ላይ ለተደረገ ጥሰት ትኬት ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በኢንትረኔት(ኦንላይን) እንደገና እንዲታይሎት አቤቱታ ማስገባት ይችላሉ። እንደገና እንዲታይሎት የሚያቀርቡት አቤቱታዎ የዳኝነት ውሳኔ ከተሰጠበት አንስቶ ባለው በ 30 የመቁጠሪያ(ካላንደር) ቀናት ውስጥ ለዲኤምቪ (DMV) መድረስ አለበት። ጥያቄዎ ከሚከተሉት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ምክንያት ላይ መመስረት አለበት:

1.    አዲስ የታወቀ ወይም አዲስ ሊገኝ የቻለ ጠቃሚ ማስረጃ፣
2.   መከላከያውን ለመደገፍ ተጨማሪ ማስረጃ አስፈላጊነት፣
3.   በዳኝነት ሂደቱ ላይ በዳኝነት መርማሪው ተፈጽሞ ሊሆን የሚችል ስህተት፣  የዳኝነት መርማሪው ውሳኔያቸውን ያሳረፉበት ፍሬ ነገር ያለማስረጃ ሳይቀበል(ጁዲሻል ኖቲስ ሳያደርግ) መቅረት ወይም የዳኝነት መርማሪው ውሳኔያቸውን ያሳረፉበት ያለማስረጃ የተቀበሉትን ፍሬ ነገር ለመልስ ሰጭው ሳያሳውቁ ሲቀሩ የመሳሰሉትን ጨምሮ፤ ወይም
4.  ጭብጥ ነገሮቹ ላይ በተጨማሪ መነጋገር አስፈላጊ ሲሆን።

እንደገና ይታይልኝ የሚሉት ጥያቄዎ እንደገና መታየቱን የሚደግፉ ሁሉኑን ሰነዶቹን እና ማስረጃዎቹን (ማለትም፣ የተሽከርካሪ ምዝገባ፣ ፎቶግራፎችን፣ ወዘተ) ማካተት አለበት። እንደገና ይታይልኝ የሚሉት ጥያቄ ከተከለከለ፣ እንደገና ይታይልኝ ያሉት ከተከለከለበት አንስቶ ባለው በ 30 የመቁጠሪያ (የካላንደር) ቀናት ውስጥ ለትራፊክ ዳኝነት ይግባኝ ቦርድ (Traffic Adjudication Appeals Board) ይግባኞን ማስገባት ይችላሉ።

እንደገና ለመታየት ብቁ የማይሆኑበት ልዮ ሁኔታ።  ውሳኔው እንዲነሳሎት አቤቱታ(Motion to Vacate) አቅርበው አቤቱታዎ ዳኝነቱን በወሰኑት መርማሪ ውድቅ ከሆነ፣ እንደገና ይታይልኝ የሚል ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም። ውሳኔው ይነሳልኝ የሚለው ጥያቅ ውድቅ ሆኖ ከሆነ በቀጥታ ለትራፊክ ዳኝነት ይግባኝ ቦርድ (Traffic Adjudication Appeals Board) ተጨማሪ ዳኝነት ይደረግ እንደሆነ ለመጠየቅ ይግባኝ ማለት አለቦት።

እንደገና ይታይልኝ የሚለውን  ጥያቄዎን እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ።  እንደገና ይታይልኝ የሚለው ጥያቄዎ በኢንተርኔት(ኦንላይን) በዲኤምቪ (DMV) ድህረ-ገጽ በኩል ወይም በፖስታ መቅረብ አለበት። ተሽከርካረዎ ተቆልፎ(ቡት ተደርጎ) ወይም ተጎትቶ ተወስዶ(ቶው ተደርጎ) ካልሆነ በስተቀር፣ ወይም በንጹህ እጅ(ክሊን ሀንድስ) ህግ መሰረት (ማለትም፣ ያልተከፈለ እዳ ስላለቦት የዲኤምቪን(DMV) አገልግሎት ለመጠቀም አለመቻል)  ፈቃድ ወይም ታርጋ ማግኘት ካልቻሉ በስተቀር እንደገና ይታይልኝ የሚለውን ጥያቄዎን በአካል ማቅረብ አይችሉም።

እንደገና እንዲታይሎት በኢንተርኔት(ኦንላይን) ያቅርቡ

• እንደገና ይታይልኝ የሚል ጥያቄ በኢንተርኔት(ኦንላይን) ሊቀርብ ይችላል። 
• ጥያቄዎ ጥፋተኛ ያደረጎት ዳኝነት ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ ባለው በ 30 የመቁጠሪያ(ካላንደር) ቀናት ውስጥ መድረስ አለበት።
• እላይ ከተዘረዘሩት አራት ምክንያቶች ውስጥ አንዱን ወይም ከአንድ በላይ በሆኑት ምክንያቶች ላይ በመመርኮዝ ክርክሮን አጠቃለው በኢንተርኔት(ኦንላይን) የማመልከቻ ቅጽ ይሙሉ። ቅጹን ያስገቡ እና በመጀመሪያው ዳኝነት ላይ ያልቀረበን ማንኛውም ማስረጃ ወደላይ ይጫኑ(አፕሎድ ያድርጉ)። 
• ወደሰጡት የኢሜል አድራሻ የኢሜል ማረጋገጫ ይሰጣል። የማረጋገጫ ደረሰኙን  በኢሜል ካልደረሶት፣ እንደገና ይታይልኝ የሚለው ጥያቄዎ አልደረሰንም ማለት ነው፣ እናም በኢንተርኔት(ኦንላይን) ወይም በፖስታ እንደገና ማስገባት ይኖርቦታል ማለት ነው።
• የዳኝነቱ መርማሪው እንደገና ይታይልኝ ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ላይ በ180 የመቁጠሪያ(ካላንደር) ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል። 

እንደገና ይታይልኝ የሚለውን ጥያቄ በፖስታ ያቅርቡ

• ጥያቄዎ ጥፋተኛ ያደረጎት ዳኝነት ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን አንስቶ ባለው በ 30 የመቁጠሪያ(ካላንደር) ቀናት ውስጥ መድረስ አለበት።
• እላይ በተዘረዘሩት አራት ምክንያቶች ውስጥ አንዱን ወይም ከአንድ በላይ በሆኑት ምክንያቶች ላይ በመመርኮዝ ክርክሮን አጠቃለው እንደገና እንዲታይ መጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ ። በመጀመሪያው ዳኝነት ላይ ያልቀረበን ማንኛውም ማስረጃ ያያይዙ።
• ወደሚከተለው በፖስታ ይላኩ:

        DMV Adjudication Services
        Attn: Request for Reconsideration
        PO Box 37135
        Washington, DC 20013

ስለ ትኬትዎ የተሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ መጠየቅ <<back to top>>

የዳኝነት መርማሪን ውሳኔ ይግባኝ ለማለት ቢፈልጉ፣ ከትራፊክ የዳኝነት የይግባኞች ቦርድ (Traffic Adjudication Appeals Board) ዘንድ ይግባኝ ማስገባት(ፋይል ማድረግ) አለቦት። እንዴት አድርገው ይግባኝ ማስገባት (ፋይል ማድረግ) እንደሚችሉ የሚጠቁም ዝርዝር መመርያዎች በይግባኝ ማመልከቻ ቅጽ ላይ ተዘርዝረዋል።

ይግባኝ ሊባልላቸው የሚችሉ ውሳኔዎች

የዳኝነት መርማሪው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ከማለቶ በፊት እንደገና እንዲታይሎት ጠይቀው ወይም በሌሉበት የተወሰነን ውሳኔ እንዲነሳሎት ጠይቀው ጥያቄዎ ውድቅ የተደረገ መሆን አለበት። ይሄ፣ የማቆምያ(ፓርኪንግ)፣ የፎቶ ማስፈጸሚያ፣ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የተደረገ የአነስተኛ ጥሰት ትኬቶች፣ የመንጃ ፈቃድዎ መታገድ ወይም መሻር፣ እና ውሳኔውን ለማንሳት የቀረበ አቤቱታዎ (Motion to Vacate Judgment) ውድቅ መሆን ወይም ለተወሰኑ ጉዳዮች የሚያገለግል የስራ ነክ ፈቃድ ጥያቄዎ (Request for a Limited Occupational License) መከልከልን  ያጠቃልላል።  

ይግባኝ መቼ ማለት እንደሚቻል 

እንደገና ይታይልኝ ከሚለው ወይም ይነሳልኝ ከሚለው አቤቱታ ቀን አንስቶ ባለው በ 30 የመቁጠርያ (ካላንደር) ቀናት ውስጥ ይግባኞ ለዲኤምቪ (DMV) መድረስ አለበት።

ይግባኝ እንዴት እንደሚባል (ፋይል እንደሚደረግ)

ይግባኝ ለማለት (ፋይል ለማድረግ)፣ መጀመርያ የይግባኝ ማመልከቻ ቅጽ (Appeals Application Form) መሙላት ያስፈልጎታል። ለያንዳንዱ ይግባኝ ለተባለበት ትኬት የትኬቱን የገንዘብ ቅጣት፣ ማንኛውንም መቀጫዎች እና $10 የይግባኝ ክፍያ መክፈል ይኖርቦታል። ይግባኝ የሚሉት (ፋይል የሚያደርጉት)፣  በመንቀሳቀስ ላይ እያለ ለተደረገ አነስተኛ ጥሰት ትኬት ላይ፣ ወይም የመንጃ ፈቃድዎ ወይም በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ የመንዳት እድሎ(ፕሪቪሎጆ) መታገድ ወይም መሻር ላይ ከሆነ፣ በተጨማሪ $50 በጹሁፍ ግልባጭ ማድረጊያ (የትራንስክሪፕት) መያዣ ክፍያ (ትራንስሪፕት ዲፖሲት ፊ) መክፈል አለብዎት። ማሳሰብያ፡ መያዣው የትራንስክሪፕቱን ዋጋ የማይሸፍን ከሆነ፣ ተጨማሪ ክፍያ ክፈሉ ይባላሉ። የመያዣ ክፍያው (ደፖሲት ፊ) ከትራንስክሪፕቱ ዋጋ የበለጠ እንደሆነ፣ ልዩነቱ ተመላሽ ይሆንሎታል። የይግባኝ ቦርዱ (The Appeals Board) በመጀመሪያ ዳኝነት የቀረቡ እንደነ ትኬት፣ ምስክርነት፣ ማስረጃ እና የዳኝነት ሂደቱ የጽሑፍ ግልባጭ (hearing transcript) ግምት ውስጥ ያስገባል። በይግባኝ ቦርዱ ፊት በአካል አይቀረብም። በተጨማሪ፣ በመጀመርያው ዳኝነት ወቅት ያልቀረበ ተጨማሪ ሰነዶች ወይም ማስረጃዎች ማቅረብ አይችሉም።

ጉዳዮን በይግባኝ ካሸነፉ

የይግባኝ ቦርዱ የዳኝነት መርማሪውን ውሳኔ ከሻረው፣ ሁሉም የገንዘብ ቅጣቶች፣ መቀጮዎች እና ክፍያዎች ወደርሶ ተመላሽ ይሆናሉ።

ሌሎች የዳኝነት አገልግሎቶች መረጃ  <<back to top>>

በመንቀሳቀስ ላይ እያለ ለተደረገ አነስተኛ ጥሰት ዳኝነት ቀጠሮ ማስያዝ፣ የመቆለፍ (ቡት የመደረግ)/ጎትቶ መውሰድ (ቶው መደረግ) መረጃ፣ መሻሮች/መታገዶች፣ ወዘተ ለመሳሰሉት፣ ሌላ ለማንኛውም ተጨማሪ የዳኝነት አገልግሎቶች መረጃና እርዳታ ለማግኘ በ 311 (202-737-4404) ይደውሉ።

የዳኝነት ሂደቱን ለማካሄድ እገዛ ካስፈለጎት ወይም ከዳኝነት ሂደቱ ጋር የተዛመተ ቅሬታ ካሎት እባኮን የትኬት ዳኝነት እንባ ጠባቂን (Ticket Adjudication Ombudsman) በ [email protected] ወይም 202-729-7092 ያግኙ።

የዳኝነት አገልግሎቶች ቦታ እና ሰዓታት ከታች ተጠቁመዋል፡

          DC DMV
          Adjudication Services
          301 C Street, SW
          Washington, DC 20001

          ስልክ፡  311 or 202-737-4404

          ያለ ቀጠሮ በመሄድ ለሚደረጉ ዳኝነቶች፡  ሰኞ - ዓርብ፣ 8:15am – 4pm
          የትኬት፣ መቆለፍ (ቡት መደረግ) እና የመጎተት (ቶው መደረግ) ክፍያዎች፡ ሰኞ - ዓርብ፣ 8:15am-5pm

          በዳኝነት ቦታ ያለውን የደምበኞች ብዛት ለማየት እዚህ ይጫኑ

የዳኝነት ቅጾች እና የኦንላይን (የኢንተርኔት) ግብይቶች(ማስፈጸሚያዎች) <<back to top>>

የዳኝነት የውክልና ስልጣን ቅጽ 
የይግባኝ ቅጽ
ውሳኔ ይነሳልኝ የሚል አቤቱታ ሂደት ማብራሪያ ቅጽ
የማቆሚያ(ፓርኪንግ) ያለቀጠሮ ዳኝነት መስሚያ ማብራሪያ ቅጽ
የፎቶ ማስፈጸሚያ ያለቀጠሮ ዳኝነት መስሚያ ማብራሪያ ቅጽ
የፓስታ ዳኝነት ቅጽ
ውሳኔን ለማስነሳት የአቤቱታ ቅጽ
እንደገና ይታይልኝ ብሎ መጠየቂያ ቅጽ
የኦንላይን (የኢንተርኔት) ዳኝነት ጥያቄ
የማቆምያ(ፓርኪንግ)/ፎቶ ትኬቶች መክፈል
በመንቀሳቀስ ላይ እያለ ለተገኘ ትኬቶች መክፈል

የታረመበት:  ኤፕሪል 12፣ 2015