Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dmv

Department of Motor Vehicles
 

DC Agency Top Menu

-We are experiencing a system error that is causing duplicate refund checks to be issued to some DMV customers erroneously. If you have been affected by the glitch, to quickly resolve this matter please deposit or cash one check and destroy the other. If you attempt to cash the second check, it will not be honored by the bank.
We apologize to all DMV customers for the inconvenience as we diligently work to rectify this issue.

 

-DC DMV will no longer prevent DC residents from applying for a new or renewed driver license because of failing to meet the requirements of the Clean Hands Law.

-A +A
Bookmark and Share

አዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQs)

አዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQs)

  1. የአዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! ማስረጃ ምንድን ነው?
  2. የአዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! ማስረጃ የሚገኘው መቼ ነው?
  3. የአዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! ማስረጃ ምን ያህል ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?
  4. የDC DMV REAL ID የመንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ለማግኘት ምን ይዤ መምጣት አለብኝ?
  5. የአሁኑ የዲሲ መንጃ ፈቃዴ/መታወቂያ ካርዴ አሁንም ይሰራል?
  6. የማህበራዊ ዋስትና ካርዴን ማሳየት አለብኝ? ከሌለኝስ?
  7. በመንጃ ፈቃዴ/ መታወቂያ ካርዴ ላይ ያለው ኮከብ ምን ማለት ነው?
  8. የመንጃ ፈቃዴን ወይም መታወቂያ ካርዴን በመስመር ላይ ወይም በ DC DMV የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ማደስ እችላለሁ?
  9. በመንጃ ፈቃዴ ወይም በመታወቂያ ካርዴ ላይ አድራሻዬን መለወጥ የምችለው እንዴት ነው?
  10. በመንጃ ፈቃድ ወይም በመታወቂያ ካርድ ላይ ስሜን እንዴት መቀየር እችላለሁ?
  11. የመንጃ ፈቃዴ ወይ መታወቂያ ካርዴ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
  12. ክፍያዎቹ ስንት ናቸው?
  13. የአካል፣ የአይን እና የህብረ ህዋስ ለጋሽ ከሆንኩ፣ ያ በመንጃ ፈቃዴ ወይም መታወቂያ ካርዴ ላይ ይታያል?
  14. የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ለመንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ወታደራዊ መለያ ይሰጣል?
  15. የድሮው የዲሲ ማስረጃ ንድፍ አለኝ እና ወደ አዲሱ ንድፍ መለወጥ እፈልጋለሁ? ያንን ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?

ጥያቄ 1: የአዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! ማስረጃ ምንድን ነው?

የአዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! ማስረጃ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት አዲሱ የመንጃ ፈቃድ እና የመታወቂያ ካርድ ንድፍ ነው፣ ይህም የማጭበርበር ሙከራዎችን ለመቀነስ አሁን ካለው ማዕከላዊ የአሰጣጥ ሂደት ጋር፣ የተሻሻሉ የጥበቃ ባህሪያትን ያካትታል። አዲሱ ንድፍ የቼሪ አበባዎችን፣ የዉድ ትረሽ ወፍን እና የፍሬድሪክ ዳግላስ መታሰቢያ ድልድይን የሚያካትቱ ደማቅ ቀለሞች እና የቅጥ አማራጮችን ያሳያል።

ጥያቄ 2፡- የአዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! ማስረጃ የሚገኘው መቼ ነው?

ከሰኞ ጁላይ 17፣ 2023 ጀምሮ የዲሲ ሞተር ተሸከርካሪዎች መምሪያ (DC DMV) አዲስ የመንጃ ፍቃድ እና የመታወቂያ ካርድ ንድፍ ለአዲስ አመልካቾች መስጠት ይጀምራል።

ጥያቄ 3፡- የአዲስ እይታ፣ አዲስ ጥበቃ፣ እርስዎ! ማስረጃ ምን ያህል ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

ይህ አዲስ ባለ ብዙ ሌዘር ምስል (MLI) ባህሪ ለሃሰተኛ ሰዎች ለማመሳሰል አስቸጋሪ የሆነ የላቀ ደህንነትን ያመጣል እንዲሁም የማጭበርበር ሙከራዎችን ይቀንሳል።

ጥያቄ 4፡- የDC DMV REAL ID የመንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ለማግኘት ምን ይዤ መምጣት አለብኝ?

የእኛ የመንጃ ፈቃድ እና የመታወቂያ ካርድ ድረገጾች የዋሽንግተን ነዋሪዎች ለማመልከት ብቁ እንዲሆኑ እና ወደ DC DMV የአገልግሎት ማዕከል ይዘው መምጣት ያለባቸውን የማስረጃ አይነቶች ያብራራሉ። እነዚህ ሰነዶች የማንነትዎን እና የእድሜዎን ማረጋገጫ፣ ህጋዊ መገኘትን፣ የዲሲ የመኖሪያ ፈቃድ እና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርን ያቀርባሉ። ሁሉም ሰነዶች ኦርጅናል፣ የተረጋገጡ የተሻሻሉ ኦርጅናሎች ወይም በሰጪው ድርጅት የተረጋገጡ እውነተኛ ቅጂዎች መሆን አለባቸው።

ለDC DMV REAL ID ብቁ ካልሆኑ፣ ለDC DMV ለተወሰነ አላማ ለሚውል መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ጥያቄ 5፡- የአሁኑ የዲሲ መንጃ ፈቃዴ/መታወቂያ ካርዴ አሁንም ይሰራል?

አዎ። ቀዳሚው የዲሲ ማስረጃ ስሪት ላላቸው ደንበኞች ጊዜው እስኪያበቃ ድረስ የሚሰራ ይሆናል።

ጥያቄ 6፡- የማህበራዊ ዋስትና ካርዴን ማሳየት አለብኝ? ከሌለኝስ?

የእርስዎን የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር (SSN) በDC DMV DL/ID ማመልከቻ ላይ ማቅረብ አለብዎት። DC DMV SSNን በማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር (SSA) በኤሌክትሮኒክ መንገድ ያረጋግጣል። SSN ከተረጋገጠ፣ ምንም ተጨማሪ ሰነድ አያስፈልግም።

የእርስዎ SSN ካልተረጋገጠ፣ መዝገቦችዎን ለማዘመን SSAን ማነጋገር ያስፈልግዎታል።

SSN ከሌለዎት ለDC DMV ለተወሰነ አላማ ለሚውል መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ጥያቄ 7፡- በመንጃ ፈቃዴ/ መታወቂያ ካርዴ ላይ ያለው ኮከብ ምን ማለት ነው?

በመንጃ ፈቃድዎ ወይም መታወቂያ ካርድዎ በላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ያለው ኮከብ የሚያመለክተው ማስረጃዎ የREAL ID መመሪያዎችን እና የግዛት የመንጃ ፍቃድ እና የመታወቂያ ካርዶችን አስተማማኝነት እና ትክክለኛነት ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶችን የሚያከብር መሆኑን ያሳያል።

ጥያቄ 8፡- የመንጃ ፈቃዴን ወይም መታወቂያ ካርዴን በመስመር ላይ ወይም በ DC DMV የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ማደስ እችላለሁ?

በአሁኑ ጊዜ የDC DMV REAL ID (ከላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ የታተመ ኮከብ ያለው) ካለዎት፣ ሁሉንም የመስመር ላይ እድሳት መስፈርቶች እስካሟሉ ድረስ ማስረጃዎን በመስመር ላይ ወይም በድርጅቱ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ማደስ ይችላሉ።

እነዚህን መስፈርቶች የማያሟሉ ከሆነ፣ የDC DMV አገልግሎት ማዕከልን መጎብኘት እና ማንነትዎን፣ በዲስትሪቱ ውስጥ የሚኖሩ መሆንዎን እና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው መምጣት አለብዎት።

ጥያቄ 9፡- በመንጃ ፈቃዴ ወይም በመታወቂያ ካርዴ ላይ አድራሻዬን መለወጥ የምችለው እንዴት ነው?

መዝገቦችዎን ወቅታዊ ለማድረግ በተንቀሳቀሱ በ60 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ በ DC DMV የአድራሻ ላይ ለውጦችን ማዘመን አለብዎት። ያስተውሉ፦ ጊዜያዊ አድራሻ እና/ወይም የፖስታ ሳጥን እንደ መኖሪያ ቤትዎ መዘርዘር አይችሉም።
 
የአድራሻ ለውጥን ለDC DMV ለማስገባት ብዙ መንገዶች አሉ፦
  1. በመስመር ላይ፦ በአሁኑ ጊዜ REAL ID ካለዎት፣ የተጠየቁትን የመኖሪያ ፈቃድ ሰነዶችን በመስቀል እና ጥያቄዎችዎን በማስገባት አድራሻዎን በመስመር ላይ መለወጥ ይችላሉ። የማመልከቻውን ሂደት በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቁ እንዲሁም የተጠየቁ ሰነዶችን ካስገቡ በኋላ፣ DC DMV ጥያቄዎ ተቀባይነት አግኝቶ እንደሆነ ለእርስዎ ለማሳወቅ በኢሜይል ምላሽ ይሰጣል። ጥያቄዎ ተቀባይነት ካገኘ የሚፈለገውን የአድራሻ ለውጥ ክፍያ እንዲከፍሉ ይመራሉ። ክፍያው ከተከፈለ በኋላ፣ DC DMV የዲሲ መንጃ ፈቃድዎን ወይም መታወቂያ ካርድዎን፣ ከማንኛውም ተዛማጅ የተሽከርካሪ ምዝገባ ጋር ያዘምናል።

በፖስታ፦ በአሁኑ ጊዜ REAL ID ወይም ለተወሰነ አላማ የሚውል ማስረጃ ካለዎት አድራሻዎን በፖስታ መቀየር ይችላሉ። አስፈላጊዎቹን ሁለት የመኖሪያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ የተሞላ የDC DMV DL/ID ማመልከቻ ቅጽ እና ትክክለኛውን ክፍያ ወደሚከተለው አድራሻ ይላኩ፦

DC DMV

ትኩረት፥ የአድራሻ ለውጥ

PO Box 90120

Washington, DC 20090

በአካል፦ REAL ID ወይም ለተወሰነ አላማ የሚውል ማስረጃ ካለዎት፣ የእርስዎን ሁለት የመኖሪያ ፈቃድ ሰነዶች፣ የተሞላ የDC DMV DL/ID ማመልከቻ ቅጽ እና የገንዘብ ክፍያን ወደ DC DMV አገልግሎት ማዕከል ይዘው መምጣት አለብዎት።

ጥያቄ 10፡- በመንጃ ፈቃድ ወይም በመታወቂያ ካርድ ላይ ስሜን እንዴት መቀየር እችላለሁ?

ስምዎ ከተቀየረ፣ መጀመሪያ ስምዎን በማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር መቀየር ወይም ማስተካከል አለብዎት። በመቀጠል፣ በዲሲ ማስረጃዎች ላይ ስምዎን ለመቀየር፣ የDC DMV አገልግሎት ማዕከልን መጎብኘት እና የአሁኑን የዲሲ መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ከሚከተሉት ኦርጅናል ሰነዶች አንዱን ይዘው መምጣት ያስፈልግዎታል፦

  • የተረጋገጠ የጋብቻ የምስክር ወረቀት (በጋብቻ ምክንያት የስም ለውጥ)
  • የፍቺ ውሳኔ (በፍቺ ምክኒያት የስም ለውጥ)
  • ይፋዊ የ U.S. ፍርድ ቤት የስም ለውጥ ሰነድ (በህጋዊ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ምክንያት የስም ለውጥ፤ ጉዲፈቻን ጨምሮ)

ጥያቄ 11፡- የመንጃ ፈቃዴ ወይ መታወቂያ ካርዴ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

ሂደቱን ከጨረሱ እና ክፍያውን ከከፈሉ በኋላ DC DMV ጊዜያዊ የወረቀት መንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ይሰጥዎታል። ይህ ጊዜያዊ ስነድ ለ45 ቀናት ያገለግላል፤ ትክክለኛ ፍቃድዎ ወይም ካርድዎ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በፖስታ ይላክልዎታል። DC DMV ፈቃዶችን ወይም መታወቂያ ካርዶችን በፖስታ ሳጥኖች አይልክም።

ጥያቄ 12፡- ክፍያዎቹ ስንት ናቸው?

ለበለጠ መረጃ እባክዎ የክፍያዎች ድረገጻችንን ይጎብኙ።

ጥያቄ 13፡- የአካል፣ የአይን እና የህብረ ህዋስ ለጋሽ ከሆንኩ፣ ያ በመንጃ ፈቃዴ ወይም መታወቂያ ካርዴ ላይ ይታያል?

ለመንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ሲያመለክቱ የአካል፣ የአይን እና የህብረህዋስ ለጋሽ ጥያቄ መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ በመሃል ላይ “ለጋሽ” የሚል ልብ በመንጃ ፈቃድዎ ወይም መታወቂያ ካርድዎ ፊት ለፊት ይታያል።

ጥያቄ 14፡- የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ለመንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ወታደራዊ መለያ ይሰጣል?

DC DMV ለመንጃ ፈቃድ ወይም ለመታወቂያ ካርዱ የውትድርና ስያሜ ይሰጣል። ለዚህ ስያሜ ብቁ ለመሆን፣ ከUS ጦር ሃይሎች ቅርንጫፍ በክብር የወጡ መሆን እንዲሁም ለDC DMV የውትድርና ሁኔታዎን የሚያረጋግጥ የDD 214 ቅጽዎን፣ የWD AGO ቅጽዎን ወይም DD 256 ቅጽዎን ማቅረብ አለብዎት። የDC DMV የአገልግሎት ማዕከልን በመጎብኘት እና የተጠየቀው ሰነድ በማቅረብ ስያሜውን መጠየቅ ይችላሉ።

ጥያቄ 15፡- የድሮው የዲሲ ማስረጃ ንድፍ አለኝ እና ወደ አዲሱ ንድፍ መለወጥ እፈልጋለሁ? ያንን ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?

አንድ ደንበኛ መንጃ ፈቃዱን ወይም መታወቂያ ካርዱን ወደ አዲሱ ንድፍ መለወጥ ከፈለገ፣ ግልባጭ ማስረጃ በማግኘት ይህንን ማድረግ ይችላል።

እንዲሁም አንድ ደንበኛ ያለቦታው በመሆኑ ወይም በጉዳት ምክንያት ግልባጭ ማስረጃ ማግኘት ከፈለገ ይህ ሂደት ሊጠናቀቅ ይችላል።

ለግልባጭ ማስረጃ ክፍያ የሚጠየቅ ይሆናል